About Us

ጣቢያችን መናኸሪያ ሬድዮ 99.1 መደበኛ ስርጭቱን የጀመረው ግንቦት አንድ ቀን 2015 ዓ.ም ቢሆንም በአድማጭ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ችሏል፡፡ ጣቢያው ተቀባይነት ማግኘት የቻለው ሙያዊ ኃላፊነቱን ጠብቆ በሚሰራቸው ዘገባዎችና ፕሮግራሞች ነው፡፡ ጣቢያችን በእራሱ ከሚሰራቸው ፕሮግራሞች ባሻገር በትብብር ከተለያዩ አካላት ጋር ይሰራል፡፡

በሀገራችን በአዲስ እና ለየት ባለ አቀራረብ ወደ ሚዲያ እንዱስትሪ የተቀላቀለው መናኸሪያ ሬድዮ 99.1 በሚያነሳቸው ማህበራዊ እና ሀገራዊ ርዕሰ ጉዳዮች እንዲሁም ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዮች አማካኝነት ተደማጭነት እና ተቀባይነትን ማተረፍ ችሏል፡፡ በቀጣይ ለሀገር የሚጠቅም እና ማህበረሰብ አቀፍ ይዘት ባለቸው ርዕሰ ጉዳዮች እና መዝናኛ ፕሮግራሞች በተሻለ ብቃት እና የጥራት ደረጃ ቅርፅ በማዘጋጀት የብዙሃንን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በትጋት እየሰራ ይገኛል፡፡

ተልዕኮ

ሚዲያ በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግባሮች ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው። በተለይም እንደ እኛ ዓይነት በማደግ ላይ ለሚገኝ ሀገር ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚገባቸውን ሀገራዊ ትልሞችን በማሳወቅና በማስተማር ረገድ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ   መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1  የሀገራችንን እና የዜጎችን ትልሞች ዕውን ለማድረግ የተቋቋመ እና  በህገ መንግስቱ ላይ በግልፅ የተደነገጉት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብቶች እውን እንዲሆኑ  በተለይም ሚዲያ በሀገሪቱ የሰላም፣ የልማትና የዴሞክራሲ እመርታዎች ላይ የራሱን እሴት የሚጨምር  ህግና ስርዓትን አክብሮ የሚንቀሳቀስ እንዲሆን የሚተጋ ነው፤ 

ራዕይ

ልዩነቶች የሚስተናገዱበት የውይይት መድረክ በማመቻቸት በወሳኝ ጉዳዩች ላይ ለሚከናወኑ የብሔራዊ መግባባት ስራዎች የበኩሉን ሚና መወጣትን የሚያምን፤ከስሜታዊነት፣ ከአሉባልተኝነትና ከጭፍን ጥላቻ የራቀ የህዝብን አስተያየት የሚያስተናግድ፣ የውይይት መድረክ ሆኖ የሚያገለግልና ህግና ስርዓትን አክብሮ የሚሰራ ተቋም ነው ፤ በሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ ሙያዊ ሚናውን እየተወጣ ተግባሩን ሚዛናዊና የህዝብን ጥቅም በሚያረጋግጥ መልኩ የቃኘ በሰለጠኑ፣ አቅምና ፍላጎት ባላቸው ባለሙያዎች ተደራጅቶ እየሰራ ያለ ተቋም ነው።