ሕዳር 11 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢራን የአሜሪካን የባሕር ላይ እገዳ በቀጥታ ለመገዳደር የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን እያዘጋጀች መሆኑን እና የአሜሪካ ኃይሎች የመርከቦቹን እንቅስቃሴ ለማስቆም ወይም ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ከሆነ በባሕረ ሰላጤው ሀገራት የነዳጅ ተቋማት ላይ የአጸፋ ጥቃት እንደምትሰነዝር ማስጠንቀቋን የፋርስ ዜና ወኪል እና የመርከብ ክትትል ተቋሙ (TankerTrackers) ዘገቡ።
እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ቴህራን በመርከቦቿ ላይ የሚወሰድ ማንኛውም ወታደራዊ እርምጃ በባሕሬን፣ በኩዌት፣ በኦማን፣ በኳታር፣ በሳዑዲ ዓረቢያ እና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የሚገኙ የነዳጅ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ያደረገ ምላሽ እንደሚያስከትል አስጠንቅቃለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በባሕረ ሰላጤው አንድ መርከብ ከሌላ መርከብ ጋር በመገናኘት (Ship-to-ship transfer) የኢራንን ድፍድፍ ነዳጅ መጫን መጀመሩን TankerTrackers አስታውቋል። ይህ መርከብ ጉዞውን ማጠናቀቅ ከቻለ፣ አሜሪካ ባለፈው ሐምሌ ወር የባሕር ላይ እገዳውን ከጣለች ወዲህ የኢራንን ነዳጅ ወደ ውጭ የጫነ የመጀመሪያው መርከብ ይሆናል።
የኢራን ማስጠንቀቂያ በባሕረ ሰላጤው ቀጣና የሚገኙ የኃይል መሠረተ ልማቶችን አደጋ ላይ የሚጥልና ሰፋ ያለ ወታደራዊ ፍጥጫ ሊቀሰቅስ የሚችል ስጋት መፍጠሩ ተመላክቷል። በቀጣናው ያለው ወታደራዊ ውጥረት እንደቀጠለ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ ሰዓታት ውስጥ አዳዲስ ክስተቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
አፍሪካ ቀስ በቀስ እየተሰነጠቀች አዲስ ውቅያኖስ የመፍጠር ሁኔታዋ እየሰፋ ነው ተባለ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለዓመታት የሳይንስ ሊቃውንትን ትኩረት ሲስብ የቆየው የአፍሪካ ቀጣናዊ ለውጥ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።
አፍሪካ አህጉር ቀስ... read more
ለእንቁላል ዋጋ መጨመር የመኖ ምርት የሚመጣባቸዉ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር ዋነኛ ምክንያት ነዉ ተባለ
በመዲናዋ የእንቁላል ዋጋ ከ17 እስከ 20 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዋጋዉ እየተጋነነ መምጣቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ የዶሮ አርቢዎች እና አቀናባሪዎች... read more
በ2019 በጀት ዓመት በአንድ በመቶ የተቋማት ድጋፍ ከ6 ሺህ በላይ ሕፃናትን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዷል ተባለ
ነሐሴ 08 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናዋ ድጋፍ እና እንክብካቤ የሚያስፈልጋቸው ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይገለፃል። እነዚህን ሕፃናት ለመርዳት... read more
የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ 1.5 ሚሊየን የሚጠጉ ጎብኚዎች ወደ ላሊበላ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ
ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ ባለንበት ወርሃ ታህሳስ መጨረሻ ላይ የሚከበረዉን የገና በዓል በስፋት ከሚከበርባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የላሊበላ... read more
አላስፈላጊ የጨረር ህክምናን በማዘዝ ገንዘብ የሚቀበሉ የጤና ተቋማት አሉ ተባለ
በየሆስፒታሉ የሚገኙና ህክምና ለማድረግ የሚመጡ ታካሚዎች የጨረር ምርመራን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ የላቸውም ሲሉ ለመናኸሪያ የገለጹት በኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን የጨረርና ኒኩለር... read more
ያለ ክኒንና መርፌ በሰውነት ውስጥ መድኃኒት የሚያመርተው አስደናቂው ጥቃቅን መሣሪያ
መጋቢት 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በህክምናው ዓለም ሳይንሳዊ ልብ ወለድ የሚመስል ግን ደግሞ እውን የሆነ አዲስ ግኝት ይፋ ሆኗል። በሰሜን ምዕራብ... read more
በሩብ አመቱ 11 ሺህ የሚሆኑ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን ማሰማራት እንደተቻለ ተገለፀ
ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር የ2018 ዓ.ም... read more
በኢትዮጵያ ቋሚ የህፃናት የኩላሊት ዲያሊሲስ ህክምና መስጫ ተቋም አለመኖሩ ተገለጸ
በሃገሪቱ በኩላሊት በሽታ የተጠቁ ህፃናት ዲያሊስስ የሚያደርጉበት የህክምና መስጫ ተቋም አለመኖሩን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህፃናት ህክምና የኩላሊት ስፔሻሊስ ዶክተር... read more
አውስትራሊያ ከ16 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊዎች ዩቲዩብን ከለከለች
ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአውስትራሊያ መንግስት ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ዩቲዩብ አካውንት እንዳይኖራቸው የሚያግድ አዲስ ህግ ይፋ አድርጓል። ይህ... read more
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ... read more
ምላሽ ይስጡ