መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በጥምረት ስም ወደ ተጨማሪ ግጭት የሚያመሩ ድርጊቶችን ለሀገር አንድነትና ሰላም ሲባል ማስቆም እንደሚገባ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ሃሳባቸውን ያሳፈሩ ፓርቲዎች ተናግረዋል። ምርጫ እና ምክክር ያደረገችው ኢትዮጵያ ሰላምና አንድነቷ ተጠብቆ ሊቆይ ይገባል ሲሉ የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር መኮንን ጉላሳ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል። ዛሬም ሆነ ወደፊት እንደ ሀገር የሚጠቅመው በውይይትና በሀገራዊ አንድነት መስራት ብቻ እንደሆነ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። ሀገር በትጥቅ ትግል የምትለወጥበትና የምታተርፍበት ጊዜ አልፏል ያሉ ሲሆን፣ የጥምረት ሃይሎችን መንግስት ከህዝብ ጋር ሆኖ መቆጣጠርና ሰላምና የሀገርን አንድነት አስጠብቆ መዝለቅ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የጥምረቱ አካል ነው በማለት በማህበራዊ ሚዲያ የፓርቲያቸውን ስም ሲያነሱ የቆዩም እንዳሉ የጠቀሱት ስራ አስፈጻሚው ፓርቲያቸው ከመሰል እንቅስቃሴዎች የራቀ እና በህጋዊ መንገድ ተወዳድሮ ስልጣን አግኝቶ ህዝብን እያገለገለ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ይሁንና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ አንዳንድ ወጣቶችን አባብሎ የጥምረቱ አካል የማድረግ እንቅስቃሴዎች ሳይኖሩ እንዳልቀሩ ግምታቸዉን ገልጸዋል። ይከናወናል የተባለው ጥምረት ከገሃዱ እውነታ ጋር ሲታይ አንዳንዶቹ ፓርቲዎች እሳቤና የትግል ሃሳብ እርስ በእርሱ የሚቃረን መሆኑን ጠቁመዋል። አክለዉም የህዝብ ሰላም እንዳይነካ ሌሎች ፓርቲዎች ከፌደራል መንግስት ጎን ቆመው ሊሰሩ እንደሚገባም ስራ አስፈጻሚው አስገንዝበዋል። ህዝብ እንዲህ ባለው ያልተረጋገጠና መልክ ያልያዘ ትብብር ምክንያት ሊወሰድና የሃሳቡም ተቀባይ መሆን የለበትም ሲሉ ሃሳባቸውን የገለጹት ደግሞ የአፋር ሕዝብ ፍትሐዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አሕፍዲፓ) ስራ አስፈጻሚ አባል ሱመያ መሃመድ ናቸው። አክለዉም መንግስትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ሀገራዊ አንድነት ላይ ብቻ መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል። የታጣቂ ሃይሎችና መሰል አጎራባች ሃይሎች ጥምረት ዘለቄታዊም ህጋዊም መሰረት አለው ብለው እንደማያምኑም ጠቅሰዋል። በአፋር ክልል በኩል የጥምረቱ አካል ሆነው የቀረቡ ፓርቲዎች ስለመኖራቸው መረጃው እንደሌላቸውም አክለው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ሀገራዊ ምክክር አድርጎ ሁለንተናዊ መፍትሄ በሚሽትበት ማግስት እንዲህ ያሉ አዋኪ ጥምረቶችን በመስማት እንዳይረበሽ መንግስትና ሀገራዊ አንድነት ላይ የሚሰሩ ፓርቲዎች ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች አመላክተዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በአሰቃቂ ሁኔታ የግድያ ወንጀል በፈፀመ ወንጀለኛ ላይ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተወሰነ
መጋቢት 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ በሪሙጋ ቀበሌ በአሰቃቂ ሁኔታ የግድያ ወንጀል በፈፀመ ወንጀለኛ ላይ... read more
የምስጥ ወተት ከላም ወተት እጅግ የላቀ ገንቢነት ያለው ነው ተባለ
👉ሳይንቲስቶች ለሰው ልጅ ፍጆታ እንዲሆን እያጠኑት ነው ተብሏል
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርብ ጊዜ የተደረገ ሳይንሳዊ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የአንድ የተወሰነ የምስጥ... read more
የአለም የንግድ ድርጅት አባል መሆን ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም አለው?
https://youtu.be/yZUVVngwHcM
የአለም የንግድ ድርጅት አባል መሆን ለኢትዮጵያ ምን ጥቅም አለው?👉
read more
ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚወል ከ100 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በሰብል መሸፈኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ
ኅዳር 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በየጊዜዉ በሚከሰቱ ሰዉ ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት የተረጂ ዜጎች ቁጥር መጨመሩ ይገለጻል፡፡
በዚህም ምክንያት ከቤት... read more
ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የሚገቡ ታጣቂዎች መሳሪያቸውን ማስፈታት ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባ ተጠቆመ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) መንግስት የሃገሪቱን ሰላም ለማረጋገጥ ከታጣቂዎች ጋር የተለያዩ የሰላም ስምምነቶችን እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሰላማዊ ስምምነትን የሚቀበሉ... read more
በትግራይ ክልል በተካሄደው የ8ተኛ ክልል አቀፍ ፈተና ይሳተፋሉ ተብሎ ከተጠበቀው 50 በመቶ የሚሆኑት አለመሳተፋቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት ተማሪዎች በመደበኛ የትምህርት ሰዓት እየተማሩ አለመሆኑ እና የፈተና ሰዓትም ጠብቀዉ እየተፈተኑ... read more
ቻይና የሰውን ልጅ እርዳታ የማይሹ ሮቦቲክ ነዳጅ ማደያዎችን አስተዋወቀች
ሐምሌ 10 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና ከተሞች የሰውን ልጅ ጉልበት ሙሉ በሙሉ የሚተካ አዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ይፋ መሆኑ ተገለጸ። ይህ አዲስ... read more
ህፃን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ
አሳምነው ስዩም ታምራት የተባለ የ40 ዓመት እድሜ ያለው ግለሰብ 1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 627/1/፤/4/(ሀ) ላይ የተደነገገውን ህግ በመተላለፍ... read more
በአውስትራሊያ አንድ የሬዲዮ ጣቢያ በሚስጥር ለ6 ወራት በAI የሬዲዮ ፕሮግራም ሲያስመራ እንደነበር ተገለጸ
በአውስትራሊያ አንድ የሬዲዮ ጣቢያ ከአድማጮች “የፕሮግራም አዘጋጇ ማንነት ጥያቄ አስኪያስነሳ ድረስ በሚስጥር ለ6 ወራት ያህል ጊዜ በAI የተፈጠረች ሴት አስተናጋጅን... read more
“ባለመመካከራችን ብዙ ዋጋ ከፍለናል፤ እንመካከር”👉 ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር)
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን ዓርዓያ (ፕሮፌሰር) ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ዛሬ መጋቢት 27/2017 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የተጀመረውን... read more
ምላሽ ይስጡ