ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በኢራን የአየር ክልል ውስጥ የተመታው የአሜሪካ አየር ኃይል ኤፍ-15 ኢ ስትራይክ ኢግል ተዋጊ ጄት ፓይለት አውሮፕላኑ ከመውደቁ ጥቂት ቅጽበታት በፊት በባህር ውስጥ እንደሚኖረው «ጄሊፊሽ» ቅርጽ ያላቸው ያልተለመዱ የኢራን ድሮኖች ስብስብ ማየቱን ገለጸ። ሲኤንኤን እንደዘገበው የጄቱ መውደቅ በኢራንና በአሜሪካ መካከል እየተካሄደ ባለው ግጭት የመጀመሪያው የአሜሪካ ተዋጊ አውሮፕላን የውጊያ ኪሳራ ሆኖ ተመዝግቧል።
ፓይለቱና የጦር መሳሪያ ቁጥጥር መኮንኑ በዛግሮስ ተራሮች ላይ በተካሄደ አደገኛ የአሜሪካ ልዩ ኃይል ፍለጋና ማዳን ዘመቻ በሰላም ከተረፉ በኋላ ለደህንነት ባለስልጣናት በሰጡት የምስክርነት ቃል በሰማይ ላይ «የድሮን ፈንጂ ቀጠና» የነበረ ይመስል እንደነበር አስረድተዋል። ትላልቅ እናት ድሮኖች ከእነሱ በታች እንደ ጄሊፊሽ እግሮች የተንጠለጠሉ ትናንሽ ድሮኖችን አስከትለው በመቀናጀት በአንድነት ይንቀሳቀሱ እንደነበር የገለጸው ፓይለቱ ሁኔታውን «ልክ እንደ ባዕድ ፍጡር የሚገርም ክስተት ነበር» ሲል ገልጾታል።
ይህ ክስተት በአሜሪካ የስለላ ማህበረሰብ ዘንድ ሰፊ ክርክርና ስጋት ፈጥሯል። አንዳንድ የወታደራዊ ተንታኞች እንደሚሉት ይህ የኢራን ጄሊፊሽ መሰል የድሮን አሰላለፍ ቴክኖሎጂ «ዋን ቱ ሜኒ ሜሽድ ኔትወርኪንግ» የተባለውን እጅግ የረቀቀ የድሮን መንጋ የማዘዣ ስልት ሊያሳይ ይችላል። ይህ ቴክኖሎጂ አንድ ኦፕሬተር ወይም ዋና ድሮን በመቶዎች የሚቆጠሩ ትናንሽ ድሮኖችን በራሳቸው ፍላጎት አየር ላይ ቅርጽ ይዘው እንዲበሩና የጠላት ጄቶችን እንዲያደናቅፉ የሚያስችል ሲሆን ኢራን ይህንን አቅም ከሩሲያ ወይም ከቻይና ወታደራዊ ድጋፍ አግኝታ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል።
በሌላ በኩል አንዳንድ የአሜሪካ የስለላ ባለስልጣናት በፓይለቱ መግለጫ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ያሳስባሉ። ፓይለቱ ከአውሮፕላኑ በሚወረወርበት ወቅት በደረሰበት ከባድ የአእምሮ መናወጥና በነበረበት ከፍተኛ የውጊያ ጭንቀት ምክንያት የተፈጠረ የተሳሳተ ግንዛቤ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ የጄቱ መውደቅ ትክክለኛ መንስኤ ላይ ምርመራው መቀጠሉን አስታውቀዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ሩሲያ የድሮን ስጋትን የሚቀይር አዲስ ጥይት ሰራች
👉ከአውቶማቲክ ጠመንጃ ሲተኮስ ወደ ሦስት ተከፍሎ ድሮኖችን የሚያሳድደው “ምኖጎቶቺዬ” በጦር ሜዳ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው! ሐምሌ 03 ቀን... read more
በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ሙሉ ለሙሉ የስማርት ቆጣሪ ገጠማ መደረጉ ተገለጸ
የከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች የቆጣሪ ቅያሪ ለማድረግ እቅድ ተይዞ ሲሰራ መቆየቱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
በዚህም መሰረት በሀገሪቱ... read more
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የክህሎት ማኅበር አባል መሆኗን ተከትሎ፣ በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ የክህሎት ውድድሮች ደረጃቸውን ጠብቀው እስከ ዓለም አቀፍ መድረኮች የሚዘልቁበት ግልጽ አሠራር መዘርጋቱ ተገለጸ
ሰኔ 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ የዓለም የክህሎት ማኅበር አባል መሆኗን ተከትሎ፣ በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ የክህሎት ውድድሮች ደረጃቸውን ጠብቀው እስከ ዓለም... read more
የ12 ዓመቷ ታዳጊ የፈጠራ ስራ የዓለምን ትኩረት ሳበ፤ ለትምህርት ቤቶች የሚሆን 11.5 ሚሊዮን ዶላር በጀትም አስገኘ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በትምህርት ቤቶች ውስጥ የአየር ጥራትን ለማሻሻልና የአየር ወለድ ቫይረሶችን ስርጭት ለመቀነስ የሚረዳ ዝቅተኛ ወጪ የሚጠይቅ የአየር... read more
በትግራይ ክልል ለውሃ ማጣሪያነት የሚያገለግል ምንም አይነት ኬሚካል ባለመኖሩ እስካሁን 113 ሰው በኮሌራ ወረርሽኝ መያዙ ተገለጸ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በክልሉ አሁን ላይ ለውሃ ማጣሪያነት የሚያገለግል ምንም አይነት ኬሚካል አለመኖሩንና በከፍተኛ ሁኔታ የኮሌራ ስርጭት መበራከቱን... read more
የሽንት ቤት ወረቀት ለማግኘት ማስታወቂያ መመልከት ግዴታ ሆነ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና አንዳንድ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የሽንት ቤት ወረቀትን ለመስጠት ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ አዲስ ሥርዓት መዘርጋታቸው... read more
የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶችን የማጠናከሪያ ትምህርት ከመስጠት ባለፈ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን መፈተሸ ይገባል ተባለ
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ምንም ተማሪ ለማያሳልፉ 700 ያህል... read more
ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር ገምግሞ በቀጣይ አቋሙን ይፋ እንደሚያደርግ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ገለጸ
ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በግንቦት ወር ይካሔዳል በተባለው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ፤ ምርጫ ለማካሄድ አስቻይ ሁኔታ ስለመኖሩ በዝርዝር ገምግሞ አቋሙን... read more
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በትራፊክ ቅጣት በዓመት ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣውን ወጪ የሚያስቀር አዲስ ሶፍትዌር አስመረቀ
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን በትራፊክ ቅጣት በዓመት ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣውን ወጪ የሚያስቀር አዲስ ሶፍትዌር አስመረቀ
ታኅሳስ 24 ቀን... read more
ምላሽ ይስጡ