ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ የብሄራዊ ጥቅም ማዕከል ያደረገ አዲስ የስደተኞች ፖሊስ ለማውጣት እየሰራች መሆኗን የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ የሩብ አመት አፈፃፀሙን ለውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበ ሲሆን በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ የስደተኞች ፖሊስን ለማውጣት እየሰራች እንደምትገኝና በቅርቡ ረቂቅ ፖሊሲውን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር እንደሚደረገ የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ አገልግሎት ዋና ዳሬክተር – ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን ያስታወቁት፡፡
ዋና ዳሬክተሯ በተለይም ፖሊሲውን ማዘጋጀት ያስፈለገው በዓለም ላይ የስደተኞች ጉዳይን በተመለከተ እየታዩ ያሉ ተለዋዋጭ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
እስካሁንም ሀገሪቷ የስደተኞች ፖሊስ እንደሌላትና በአዋጅ ብቻ ትመራ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይህም ፖሊሲ የሃገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም ማዕከል ያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በፊት የስደተኞች አዋጅ ሲወጣ ለስደተኞች በርካታ ድጋፎች ይደረጉ ነበር ያሉት ዋና ዳሬክተሯ አሁን ላይ ግን በተለይም ሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መነሳቱን ተከትሎ በርካታ ረጂ ተቋማት ፊታቸውን ወደዛ ማዞራቸው ስራቸው ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
አሁን ላይ ከዚህ በፊት በነበረው አሰራር አይነት መቀጠል ከባድ በመሆኑ ፖሊሲውን ማዘጋጀት ማስፈለጉን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ በሩብ አመቱ 2 ሺህ 232 ስደተኞች እውቅና እንዲያገኙ ማድረጓን 21 ሺህ 616 ጥገኝነት ጠያቂዎች በደረጃ 1 እንዲመዘገቡ 5 ሺህ 445 ስደተኞች በደረጃ 3 እንዲመዘገቡ እንዲሁም 82 ስደተኞች ደግሞ የሀገሪቷን ህግ ተላልፈው በመገኘታቸው እውቅናቸው እንዲነሳ መደረጉም ተመላክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ