ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሐመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ ጥምር ፓርቲ በሀገሪቱ በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን የምርጫ ኮሚሽን አስታወቀ።
ከ2022 ዓ.ም ጀምሮ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር ኢራቅን ሲመሩ የቆዩት አል-ሱዳኒ፣ በብሔራዊ ምርጫው 1.32 ሚሊዮን ድምፅ አግኝተዋል። ይሁን እንጂ፣ ይህ ድል ቀጣዩን መንግሥት ለመምራት የሚያስችል ወንበር እንዲያገኙ የሚያደርግ ቢሆንም፣ የሚመሩት መንግሥት ምስረታ ሂደት ግን አሁንም ግልጽ አይደለም ተብሏል።
በኢራቅ የፖለቲካ ሥርዓት መሠረት፣ አንድም ቡድን ብቻውን በፓርላማ ውስጥ ፍፁም የበላይነትን የማያገኝ በመሆኑ፣ አሸናፊው ጥምረት መንግሥት ለመመስረት ከሌሎች ተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት መፍጠርና ስምምነት ላይ መድረስ ይኖርበታል። ይህ ሂደት ብዙ ጊዜ አስቸጋሪና ወራት የሚወስድ እንደሚሆን ተመላክቷል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ