ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተጫዋቹን አክሰል ቱዋንዜቤን ጉዳት በሚገባ እንዲከታተል ሁኔታዎችን ባለማመቻቸት ወይም ባሳዩት ግዴለቅነት የተሞላበት ድርጊት ምክንያት ክስ ቀርቦባቸዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተከላካይ ተጫዋቹን አክሰል ቱዋንዜቤን ጉዳት በአግባቡ አለመያዝ እና አለመታከም በኩል ሙያዊ ሀላፊነታቸውን አጉዋድለዋል በሚል ነው ክስ የቀረበባቸው። የፍርድ ቤት ሰነድ የሚያሳየው ፣ ቱዋንዜቤ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ክለቡን 1 ሚሊዮን ፓውንድ ካሳ እንዲከፍለው በመጠየቅ ክስ መስርቷል ሲል ስካይ ስፖረት ዘግቧል።
ቱዋንዜቤ በ2023 ከዩናይትድ ጋር የነበረው ውል ከተጠናቀቀ በኋላ አሁን ወደ ኢፕስዊች ታውን በማቅናች ክለቡን የተቀላቀለ ሲሆን፣ ክሱ የሚያተኩረው ተጫዋቹ በደረሰበት የጀርባ ጉዳት ላይ ነው። ክሱ ክለቡ በጉዳቱ አያያዝ ቸልተኝነት አሳይቷል እና በወቅቱ ተገቢውን ህክምና ባለመስጠቱ ተጫዋቹ የሙያ ዕድገቱን እና የገቢ ምንጩን እንዳሳጠመው ጠቅሷል።
የቱዋንዜቤ ጠበቆች፣ ተጫዋቹ በጉዳቱ ምክንያት በሰርካታ ጊዜ ከሜዳ ለመራ መገደዱን እና ይህም በሌሎች ክለቦች የመታየትና የመዘዋወር እድሉን እንዳሳጣው በመጥቀስ ክስ አቅርበዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ክሱን በይፋ አልተቀበለም። የክለቡ ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፤ ነገር ግን ክለቡ በህጋዊ መንገድ ጉዳዩን እንደሚከታተለው ተገልጿል። ይህ ክስ በክለቡ እና በቀድሞ ተጫዋቹ መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩን በግልፆ የሚያሳይ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ