ህዳር 01 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በማረሚያ ተቋማት እየተሰራ ያለው የእድሳት ስራ የሚበረታታ መሆኑን የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አሸነፈች አበበ ገልጸዋል።
የተቋማቱ የጽዳት ሁኔታ የተሻሻለ መሆኑንና በተለይም የሴት ታራሚዎች ክፍል በተሻለ መልኩ እድሳት እየተደረገለት መሆኑን አስታውቀዋል።
ማረሚያ ተቋማቱ ለታራሚዎች ምቹ እንዲሆኑ ከሚሰራው የእድሳት ስራ በተጨማሪ፣ ከወላጆቻቸው ጋር አብረው የሚታሰሩ እና እዚያው የሚወለዱ ህጻናትን የተመለከተ የህግ ማዕቀፍ እንደሌለ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ግን ልዩ የህግ ማእቀፉ እየተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል።
ህጻናቱ ባላጠፉት ጥፋት ከወላጆቻቸው ጋር መታሰራቸው በወደፊት ህይወታቸው ላይ የሚያደርሰውን የስነ-ልቦና ጫና በመረዳት ህጉ እንዲሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።
ችግሩን ለመቅረፍ በተደረገው ጥረት አሁን ላይ በማረሚያ ተቋማት ለሚወልዱት ህጻናት የክሊኒክ አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉን ገልጸው፤ በተጨማሪም ከ1ኛ እስከ 4ኛ ክፍል የሚማሩበት ትምህርት ቤት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
በዚህም ከሌሎች ህጻናት ተማሪዎች ጋር አብረው የሚማሩንበትን ሁኔታ መፍጠር መቻሉን ነው ያመላከቱት።
የማረሚያ ተቋማቱ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳለባቸው የገለጹት ምክትል ፕሬዝዳንቷ፤ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የጀመራቸውን ስራዎች በክልሎች ለማስፋፋት በእቅድ መያዙን አብራርተዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ