ጥቅምት 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢንዶኔዥያ ዋና ከተማ ጃካርታ በሚገኝ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መስጊድ ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት በተከሰቱ በርካታ ፍንዳታዎች ምክንያት ቢያንስ 54 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘገቡ።
የአደጋው ቦታ የከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ሲሆን፣ ፍንዳታዎቹ የተከሰቱት በዕለቱ ከሰዓት በኋላ በነበረው የጸሎት ሰዓት አካባቢ መሆኑ ተገልጿል። በደረሰው ጉዳት በርካታ ተማሪዎችና የመስጊዱ ምዕመናን የተካተቱ ሲሆን፣ ቆስለው ሆስፒታል ከገቡት ሰዎች መካከል የብዙዎቹ ጤና ሁኔታ አሳሳቢ አይደለም ተብሏል።
የጸጥታ ኃይሎች ፍንዳታዎቹን ተከትሎ ወደ ስፍራው በፍጥነት በመድረስ ምርመራ የጀመሩ ሲሆን፣ ፍንዳታዎቹ በምን ምክንያት እንደተከሰቱ እስካሁን ግልጽ የሆነ መረጃ አልተገኘም።
የፖሊስ ባለሥልጣናት ፍንዳታዎቹ በአጋጣሚ የመጣ የቴክኒክ ችግር ይሁን ወይም ሆን ተብሎ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑን ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ በሰጡት መግለጫ፣ የፍንዳታው ምንጭ በቦምብ ወይም በሌሎች ፈንጂዎች አማካኝነት ስለመሆኑ ለማወቅ የቦታውን ማስረጃዎችና ቅሪቶች በመሰብሰብ ላይ እንደሆኑ ገልጸዋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ