👉በሳይንቲስቶች ዘንድ የሐዘን መግለጫ ተብሎ የተፈረጀው የኦርካዋ ታሪክ
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በእንስሳት ዓለም ውስጥ በእናትና በልጅ መካከል ያለውን ልዩ ትስስር የሚያሳይ እጅግ ልብ የሚነካ ታሪክ በፓሲፊክ ውቅያኖስ ተመዝግቧል። ታህለኳህ (Tahlequah) ወይም በሳይንስ ስሟ J35 የምትታወቀው አንዲት የኦርካ ዝርያ የሞተውን ግልገሏን ለ17 ተከታታይ ቀናት ያህል በግንባሯ እየገፋችና እየተሸከመች ከ1,600 ኪሎሜትር በላይ መጓዟ ተዘግቧል።
ይህ አሳዛኝ ሁኔታ የተከሰተው በ2018 ዓ.ም. ሲሆን፣ ግልገሏ ከተወለደ ከሰዓታት በኋላ ሕይወቱ አልፏል። እናትየዋ ግን የልጇን ሞት ለመቀበል ባለመፈለጓ፣ የሟች ግልገሏን አስከሬን በመያዝ በውቅያኖስ ላይ ረጅም ጉዞ አድርጋለች ነው የተባለው።
የውቅያኖስ ተመራማሪዎች ይህንን ኦርካዋ ያሳየችውን ተግባር በቅርብ በመከታተል፣ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የተራዘመ የሐዘን መግለጫ እንደሆነ ገልጸውታል። የኦርካዋ ተግባር በሰሜን አሜሪካ ሰሜናዊ ምዕራብ የባሕር ዳርቻ የሚገኙት እና ለአደጋ የተጋለጡ የኦርካ እጣ ፈንታ ላይ የዓለምን ትኩረት እንዲያርፍ አድርጓል።
ታህለኳህ በመጨረሻ ከ17 ቀናት የሀዘን ጉዞ በኋላ የልጇን አስከሬን ለቅቃ ብትሄድም፣ የእርሷ ተግባር በእንስሳት ዓለም ውስጥ የእናትነት ፍቅር ምን ያህል ጥልቅና ልብ የሚነካ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ታሪካዊ ምሳሌ ሆኖ ቀጥሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ