👉ክብርን ለመጠበቅ ደፋሪን ማግባት ግዴታ ነው የተባለችው ፍራንካ ቪዮላ ማን ናት?
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዛሬ ዓመታት በፊት በጣልያን ሲሲሊ ክልል በደረሰ አንድ አሳዛኝ ክስተት ሳቢያ፣ በአገሪቱ ታሪክ ትልቅ የሕግ ለውጥ እንዲመጣ ያደረገችው የፍራንካ ቪዮላ ድፍረት አሁንም ድረስ ይወሳል።
ቪዮላ በወቅቱ ገና የ17 ዓመት ወጣት ሳለች ታግታ ከተደፈረች በኋላ፣ በወቅቱ በነበረው የሲሲሊ ባህል እና በጣሊያን ሕግ አንቀጽ 544 መሠረት፣ ቤተሰቧ እና ማኅበረሰቡ “ክብሯን ለመጠበቅ” ብላ ደፋሪዋን ማግባት እንዳለባት ጠይቀው ነበር። ይህ ሕግ ወንጀለኞች ተጎጂውን በማግባት ከቅጣት ሙሉ በሙሉ እንዲድኑ ያስችላቸው ነበር።
ሆኖም ፍራንካ ቪዮላ ይህን ጋብቻ በጥብቅ እምቢ አለች። “እምቢ” ያለችው ይህ አንድ ቃል በጣሊያን የፍትህ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሯል። የእርሷ አቋም በወቅቱ የነበረውን አሳፋሪና አድሏዊ ሕግ ለመፋለምና ለመቃወም ሰፊ የሴቶች መብት እንቅስቃሴ እንዲቀጣጠል ምክንያት ሆኗል።
የፍራንካ ቪዮላ የፍርድ ቤት ክስ ከተጠናቀቀ ከዓመታት በኋላ፣ በመጨረሻም የጣሊያን ሕግ አንቀጽ 544 በ1981 ዓ.ም. በይፋ ተሽሯል።
ታሪክ ጸሐፊዎች፣ ፍራንካ ቪዮላ የሰጠችው ድፍረት የተሞላበት “እምቢታ” የጣሊያንን ሕግ ለዘላለም የቀየረ እና ለሴቶች መብት ትግል ትልቅ ምሳሌ ሆኖ የሚያገለግል እንደሆነ ይገልጻሉ።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ