ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሩብ አመቱ 13 ሺህ 443 የሳይበር ጥቃቶችና የጥቃት ሙከራዎች መመዝገባቸውን የኢንፎርሜሽን መርብ ደህንነት አስተዳደር አስታውቋል።
አስተዳደሩ የሩብ አመት አፈፃፀሙን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የቀረበ ሲሆን በዚህ ወቅት በባለፉት ሶስት ወራት 13 ሺህ 443 የሳይበር ጥቃቶችና የጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናግረዋል፡፡
ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አለው ያሉ ሲሆን ባለፈው ተመሳሳይ ወቅት 6 ሺህ 700 ጥቃት ተሰንዝሮ እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡
የጥቃቶቹ ቁጥር ከፍ ሊል የቻለውም የኢንሳ የቁጥጥር አቅሙ ከፍ በማለቱ ምክንያት መሆኑን በማስረዳት ጥቃቶቹ ከፍተኛው ቁጥር የሚይዙት መሰረት ልማቶች ላይ ያነጣጠሩ እንደሆኑና አስቀድሞ መካለከል መቻሉን አስረድተዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ