👉 ወታደሩን ሳይጠብቅ አላርፍም ያለው የአየር ማረፊያው ዘብ
ጥቅምት 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የወታደር ዉሻ ታማኝነት አዲስ ገጽታ አየር ማረፊያ ላይ ታይቷል። አንድ ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጥ ውሻ፣ ጌታውን (ወታደሩን) በንቃት በመጠበቅ ከእግር ጥፍሩ ሳይርቅ ማንም ሳያየው በዘበኝነት ሲቆም አድሯል።
የድካም ስሜት ቢያጠቃውም ወታደሩን መጠበቁን አላቋረጠም ነው የተባለው።
ይህ ልዩ ትስስር እና ፍቅር በቃላት ሊገለጽ የማይችል ሲሆን፣ ከውሻው የወጣው ታማኝነት በስልጠና ብቻ ሊገኝ የማይችል መሆኑን ያሳያል።
ዉሻዉ ወታደሩ በእረፍት ላይ እያለ፣ የድካም ስሜት እስኪጠናወተው ድረስ ሳይተኛ በአጠገቡ በንቃት ቆሟል።
ይህ ድርጊት ከፍቅርና ከትስስር የሚመጣ ታማኝነት መሆኑንና በሥልጠና ብቻ የሚገኝ እንዳልሆነ ስሜትን የሚነካ መልዕክት አስተላልፏል።
ለዚህ ታማኝነት ያለምንም ሽልማት ወይም ጭብጨባ፣ በጸጥታና በትህትና የሚሰጥ የልብ ወዳጅነት ማሳያ ተደርጎ ቀርቧል።
ታማኝነትና ፍቅር አንዳንድ ጊዜ በአራት እግሮች እና በጀግና ልብ እንደሚመጣ አስታዋሽ መሆኑ ተገልጿል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ