መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የእድሜ ባለፀጋዎች ብዛት አንዷ የሆነችው ጃፓን፣ አረጋውያን ሠራተኞቿን በሥራ ገበታቸው ላይ ረዘም ላለ ጊዜ ለማቆየት ወደ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ እየዞረች ነው።
አረጋውያን ሠራተኞች ከባድ ሸክሞችን በቀላሉ እንዲያነሱ፣ የአካል ጉዳት ስጋትን እንዲቀንሱ እና በሥራ ቦታ ንቁ ሆነው እንዲቆዩ ለመርዳት የሮቦት ኤክሶስኬሌተን ልብሶችን (Robotic Exoskeletons) መጠቀም ጀምራለች።
እነዚህ ዘመናዊ ልብሶች የሰውን የሰውነት እንቅስቃሴ በመለየት በሞተር የሚንቀሳቀስ ድጋፍ ይሰጣሉ። ይህም በመጋዘኖች እና በኮንስትራክሽን ቦታዎች ላይ ያሉትን ሥራዎች ቀላል፣ አስተማማኝ እና ለሁሉም ዕድሜ የሚመች ያደርጋቸዋል ተብሏል።
ከፓናሶኒክ (በንዑስ ድርጅቱ አቶውን) እስከ ሳይበርዳይን ያሉት የጃፓን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ ፈጠራ ጀርባዎ ላይ ድጋፍ ሲሰጥ፣ ዕድሜ ቁጥር ብቻ መሆኑን በተግባር እያረጋገጡ ነው። እነዚህ ልብሶች የሰውነት ድካምን በመቀነስ፣ አረጋውያን “በጥበብ እንዲሠሩ፣ በጠንካራ እንዲያነሱ እና ረጅም ዕድሜ እንዲኖሩ” ይረዳሉ ተብሏል።
በጌታሁን አስናቀ
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ