መስከረም 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ውሾች ከሰው ልጅ እጅግ የላቀ የሆነ የማሽተት ችሎታ ያላቸው መሆናቸውን ሳይንሳዊ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአፍንጫቸው ውስጥ እስከ 300 ሚሊዮን የሚደርሱ የማሽተት ተቀባይ ህዋሳት የተገጠሙላቸው በመሆኑ፣ ለሰው ልጅ ፈጽሞ የማይታዩ ሽታዎችን የመለየት ብቃት አላቸው ተብሏል።
ይህ ኃይለኛ ባዮሎጂያዊ ክህሎት የሰለጠኑ ውሾች አደንዛዥ ዕፆችን፣ ፈንጂዎችን እና አልፎ ተርፎም እንደ ካንሰር እና የስኳር በሽታ (ዲያቤቲስ) ያሉ በሽታዎችን በከፍተኛ ትክክለኛነት ለይተው እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ውሾች በሰውነት ውስጥ ባሉ ጥቃቅን የኬሚካል ለውጦች አማካኝነት ጤናማና በበሽታ የተጠቁ ናሙናዎችን መለየት ይችላሉ።
ይህ አስደናቂ ግኝት በአሁኑ ወቅት የውሾችን አፍንጫ አርአያ ያደረጉ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር በሽታዎችን ቀድሞ ለመለየት የሚያስችሉ አዳዲስ ምርምሮችን በማነሳሳት ላይ ይገኛል።
በመሆኑም ውሾች በዘመናዊ የደህንነት እና የሕክምና ዘርፎች ወሳኝ አጋር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ