መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህንን ያለው የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ነው። ከሰሞኑ የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በነዳጅ ሀይል የሚሰሩ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ከዚህ በኋላ ወደ ሀገር ውስጥ እንደማይገቡና በምትኩ በጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ለሚያስገቡ የቀረጥ ነፃ እድል ይሰጣቸዋል ማለታቸው ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚያስችለውን የመጀመሪያውን ዙር የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ባስመረቁበት መድረክ ላይ እንዲህ የገለጹት።
መናኸሪያ ሬዲዮ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘዉዱን ስለጉዳዩ አነጋግሯል።
አቶ ሰለሞን በጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማብዛት ሀገሪቱ ለነዳጅ ፍጆታ የምታወጣውን ወጪ መቀነስ የሚያስችል ነው ብለዋል። በተለይ በዘርፉ ለተሰማሩ ሙያተኞች ምቹ እድል የሚፈጥር ሲሆን የነዳጅ ምርትን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ድንበር አቋርጠው ለሚጓዙ አሽከርካሪዎች ጠቀሜታ እንዳለውም አክለዋል።
ሀገሪቱ በከፍተኛ ድጎማ ወደ አገር ውስጥ ከምታስገባቸው ምርቶች ነዳጅ ዋነኛው በመሆኑ፤ በዘርፉ ላይ ያለውን ውጥረትም ይቀንሳልም ብለዋል። እንዲሁም ለምርቱ በየጊዜው የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬ መጠን በመቀነስ ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ማምጣት የሚቻልበት ስለመሆኑም አመላክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከዚህ ቀደም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች ኢትዮጵያ የራሷን ጋዝ እያመረተች እንደምትገኝ እና የምክር ቤቱ አባላት ከእረፍት ሲመለሱ በይፋ ስራው እንደሚጀምር መግለፃቸው የሚታወስ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ