መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በዛሬው ዕለት 6ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተከናወነ ሲሆን መድረኩን መክፈት የቻሉት የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ታዬ አጽቀስላሴ ናቸው፡፡
በመድረኩ ባደረጉት ንግግርም የኢትየዮጵያ የኢኮኖሚ መጠን በ2017 ዓ.ም የ8.8 በመቶ እድገት ማስመዝገብ የቻለበት ሁኔታ እንዳለም ነው ያስታወቁት፡፡ፕሬዝዳንቱ የሁለቱን ምክር ቤቶቸ በይፋ ወደ ስራ በገባበት ወቅት ኢትዮጵያ በርካታ ስራዎችን ባከናወነችበት ወቅት በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ለዚህም የታላቁ የህዳሴ ግድብን ጨምሮ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ስራ ወደ ተግባር በመግባቱ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
አክለው ባለፉት ጊዜያት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማዋቅራዊ ተግዳሮቶች መለፉን ተከትሎ በከፍተኛ እዳ ውስጥ ሀገሪቱ እንድትዘፈቅ ያደረገበት ሁኔታ እንዳለ ጠቁመው፤በአሁኑ ሰዓት በተደረጉ የማክሮ ኢኮኖሚ መሻሻያ ለውጦችን ሳቢያ የኢኮኖሚ መዛባቶችን መቀነስ የተቻለበት እና ማስተካከል የተቻለበት ሁኔታ እንዳለ ጠቁመው፤በዚህም የውጭ ምንዛሬንም ሆነ የወጪ ገቢ ስራዎች ላይም ለውጥ ማምጣት የተቻለበት ሂደት እንዳለም አንስተዋል፡፡
በዚህም ሀገሪቱ ከነበረችበት የእዳ ጥገኝነትን በመላቀቅ ኢኮኖሚያዊ ሉዋላዊነትንም ማግኘት የቻለችበት ሂደት በመኖሩ ምክንያት ከእዳ ጫና በመላቀቅ እና ወደ አምራችነት የመቀየር ስራ እንዲሰራም አጋዥ አድርጓል ሲሉ አስታውቀው፤በዚህም ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም የ8.8 በመቶ ያህል እድገት ማስመዝገብ የቻለችበት ሁኔታ እንዳለም አስታውቀዋል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ