መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና የምርምር ተቋማት የኃይል አቅርቦትን ትርጉም የሚቀይር አስደናቂ ግኝት ይፋ አደረጉ። በቤታቮልት (Betavolt) እና በሰሜን ምዕራብ መደበኛ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተገነባው ቤታቮልቲክ ባትሪ (Betavoltaic Battery)፣ እስከ 100 ዓመታት ያለማቋረጥ ኃይል የማመንጨት አቅም (ባትሪው ለ100 ዓመታት ወይም ከዚያ በላይ ሊቆይ እንደሚችል ) ተገልጿል።
ይህ የሳንቲም ያህል መጠን ያለው ባትሪ የሚሰራው ከራዲዮአክቲቭ መበስበስ ኃይልን በመጠቀም ሲሆን፣ ከባህላዊ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች በተለየ ምንም ዓይነት ሰንሰለት ምላሽ፣ ሙቀት ወይም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉትም።
ኃይሉን የሚያመነጨው እንደ ኒኬል-63 ወይም ካርቦን-14 ካሉ አይሶቶፖች በሚመነጩ ኤሌክትሮኖች አማካኝነት ነው።
ይህ ቴክኖሎጂ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የጸጥታ የኃይል ፍሰት የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለሕክምና አገልግሎትም ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ተብሏል።
ይህ ፈጠራ ተግባራዊ ሲሆን፣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከእነዚህም መካከል ለልብ ምት መቆጣጠሪያዎች (Pacemakers) እና ሌሎች የሰውነት ውስጥ ተከላዎች ቋሚ የኃይል አቅርቦት ይሰጣል ተብሏል።
በሩቅ ቦታዎች ላይ ላሉ ሴንሰሮች እና የጠፈር መንኮራኩሮች መሙላት የማያስፈልገው የኃይል ምንጭ ነው የተባለ ሲሆን ወደፊት ተጠቃሚዎቻቸውን ሊበልጡ የሚችሉ፣ ቻርጅ የማያስፈልጋቸው መሣሪያዎች እንዲፈጠሩ በር ይከፍታል ተብሏል።
የባትሪው የኃይል መጠን በአሁኑ ጊዜ ትንሽ ቢሆንም፣ የ 50 ዓመታት የሥራ ዘመኑ የዓለምን የኃይል አስተሳሰብና የዲዛይን ጽንሰ-ሀሳቦችን ለመለወጥ የሚችል ታሪካዊ እርምጃ እንደሆነ ታዛቢዎች ገልጸዋል።
ባትሪው ለሰውነት ተከላዎች (እንደ Pacemakers)፣ ለጠፈር መንኮራኩሮች እና ለረጅም ጊዜ የሚሰሩ ሴንሰሮች ታስቦ የተሰራ ሲሆን፣ ምንም ዓይነት የፍንዳታ ወይም የሙቀት አደጋ የለውም ተብሏል።
ይህ ቴክኖሎጂ ትንንሽ መሣሪያዎችን ያለም ቻርጅ ለበርካታ አስርተ ዓመታት በማንቀሳቀስ የኃይል አቅርቦትን ትርጉም ይለውጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ