መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወረቀትን ለማምረት ዛፎችን መቁረጥን የሚተካ አዲስ የዘላቂነት ፈጠራ ይፋ ተደርጓል። ተመራማሪዎች ሣርን ዋና ጥሬ እቃ በማድረግ፣ ለዓመታት በአካባቢ ላይ ጉዳት ሲያደርስ የነበረውን ባህላዊ የወረቀት አሠራር የሚቀይር ዘዴ መጥቀማቸው ተሰምቷል።
የዚህ አዲስ ሂደት ዋና ዓላማ የደን ሀብትን መጠበቅ ሲሆን፣ የውጤታማነትና የአካባቢ ጥቅሞቹም አስገራሚ ናቸው ተብሏል፡፡ አዲሱ የማምረቻ ዘዴ እጅግ በጣም አነስተኛ ውሃ ይጠቀማል። ሣርን ለማቀነባበር እንደ እንጨት ጠንካራ ኬሚካሎችን ስለማይፈልግ፣ አብዛኛው የማምረት ሂደት ያለ ብሊች (Bleach) ወይም በትንሽ ኬሚካል ይከናወናል ነው የተባለው።
ሣር በፍጥነት የሚያድግ እና በቀላሉ የሚሠራ በመሆኑ፣ ከባህላዊው መንገድ ያነሰ ኃይል ይፈልጋል፤ ይህም ለአካባቢ የሚኖረውን ጉዳት በእጅጉ ይቀንሳል ተብሏል።
ይህ ፈጠራ፣ በየቀኑ የምንጠቀመው ወረቀት ከጫካ ጥፋት ጋር የተያያዘ መሆን እንደሌለበት በተግባር አሳይቷል። በፈጣን ዕድገትና በቀላል ሂደት የሚገኘውን ሣር ወደ የዕለት ተዕለት ፍላጎታችን መቀየር፣ ለወደፊቱ የደን ጥበቃ ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመስጠት ትልቅ ተስፋ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ