መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቱሪዝም ዘርፉን አሁን ካለበት ይበልጥ ለማሳደግ ክልሎች መስራት እንደሚጠበቅባቸው የቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጻል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበ 5ተኛው የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በተካሄደበት መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዲህ አይነት ዝግጅት በክልል ደረጃ መካሄዱ ዘርፉን ለማሳደግና በክልሎች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ ያስችላል ብለዋል።
ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋት በኃላ የቱሪዝም ዘርፉ የተጎዳ ቢሆንም፤ በቅርቡ በተሰሩ ስራዎች ወደ ቀድሞው መመለስ መቻሉን ተናግረዋል። በ2017 ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ከዘርፉ 3 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በቀጣይ የሚገኘውን የገቢ መጠን ለማሳደግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በተለይም ክልሎች የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በሰሩት ስራ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት እያደገ መምጣቱን በመግለጽ፤ ይህን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እና ሁሉም የቱሪስት መዳረሻዎች ለጎብኚዎች ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚያስፍልግ ተናግረዋል።
ሁሉም ክልሎች በተናጠል ሲሰሩ የነበረው በዲጂታል ስርዓት የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን የማስተዋወቅ ስራ በሀገር አቀፍ ደረጃ መጀመሩ ትልቅ ለውጥ ይዞ እንደሚመጣም ነው የገለጹት።
ለ5ተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የሚሰበሰብበት መድረክ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የኦሮሚያ የቱሪዝም ኮሚሽን የእቅድ ክትትል፤ በጀትና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ሰለሞን ናቸው።
ለቱሪዝም እድገት አስተዋጸኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና የሚሰጥበትና የሚስ ቱሪዝም ምርጫ የሚካሄድበት መድረክ መሆኑን ያስታወቁት ዳይሬክተሩ፤ ከሌሎች ክልሎች ጋር ልምድ በመለዋወጥ የክልሉን የቱሪዝም ሀብት የማስተዋወቅ ስራ የሚሰራበት ነው ብለዋል፡፡
የአለም የቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያየ መርሀ ግብር እየተከበረ እንደሚገኝ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ