መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአባይ ወንዝ ከፍታው ሲጨምር የአገሪቱ መንግስት ለህዝቡ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል።
በመሆኑም አገሪቱ ትላንት ማክሰኞ በአባይ ወንዝ ዳርቻ ያለው የውሃ መጠን እየጨመረ መምጣቱን በመግለጽ ዜጎቿ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አስጠንቅቃለች።
የሱዳን የመስኖ ሚኒስቴር መግለጫ በዋድ አል-አይስ፣ በማዳኒ፣ ካርቱም፣ አትባራ፣ በርበር እና ጀበል አውሊያ በተባሉ አከባቢዎች ጎርፍ እንዳጋጠመ አስታውቋል።
በሴናር፣ አልጃዚራ፣ ካርቱም ግዛቶች እና በነጭ አባይ ዳርቻዎች ደግሞ ስጋት እንዳለ ነው ያስጠነቀቀው።
የአባይ ወንዝ እና ገባሮቹ መጠናቸው በመጨመሩ ባለፉት ሁለት ቀናት በሱዳን በሚገኙ በርካታ ክልሎች የጎርፍ አደጋ እንዳጋጠመም የአናዶሉ ዘገባ አስታውሷል።
እንደ አገሪቱ መንግስት መረጃ ከባለፈው ሰኔ 30 ጀምሮ በዝናብ እና በጎርፍ አደጋ ከ125ሺ በላይ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ሱዳን ከሰኔ እስከ ጥቅምት ባለው ወቅት ከባድ ዝናብ እንደሚያጋጥማት እና ይህም ብዙ ጊዜ ሰፊ አመታዊ የጎርፍ አደጋ እንደሚያስከትል የሚታወቅ ነው።
አገሪቱ በአባይ ወንዝ የታላቁ ህዳሴ ግድብ መገንባት የድርቅ ስጋት ውስጥ ይከተኛል ብትልም፣ ግድቡ ተሰርቶ ከተጠናቀቀም በኋላ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ አልቀረላትም።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ