መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአሜሪካ ውጪ በሚመረቱ ሁሉም ፊልሞች ላይ የ100 በመቶ ቀረጥ (ታሪፍ) ለመጣል ማቀዳቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በይፋ አሳውቀዋል። ትራምፕ ይህ እርምጃ የአሜሪካን የፊልም ኢንዱስትሪ ከውጭ ምርቶች ለመጠበቅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ከአሜሪካ ውጪ የሚመረቱ ማናቸውም እና ሁሉም ፊልሞች” ላይ የ100% ቀረጥ ለመጣል ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የፊልም ሥራው በሌሎች አገሮች “እንደ ሕፃን ከረሜላ እንደመስረቅ” ከአሜሪካ “ተሰርቋል” በማለት ከሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ ካሊፎርኒያ በአለም አቀፍ ፊልሞች መጎዳቷን ጠቅሰው፣ የካሊፎርኒያ ገዥ የሆኑትን ጋቪን ኒውሰምን ደግሞ “ደካማና ብቃት የሌላቸው” በማለት በአደባባይ ወቅሰዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የንግድ እና የፊልም ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች በዲጂታል መንገድ በሚተላለፉ ፊልሞች ላይ የ100% ቀረጥን በተግባር ማስፈጸም እንደሚቻል ወይም እንደማይቻል ጥያቄ እያነሱ ነው። ይሁን እንጂ፣ የትራምፕ ማስታወቂያ የሆሊውድን ዓለም አቀፍ የንግድ ሞዴል ሊያናጋ እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ