መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የተሻለ ኑሮና ገቢን ለማግኘት በማሰብ ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚያቀኑ የዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ እየተገለጸ ባለበት ወቅት፣ በስደት ላይ የነበሩና ወደ ሀገር ቤት ለተመለሱ ዜጎች የስነልቦና ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተካሂዷል።
ወደ ውጭ የሚሄዱ ዜጎች በሚያቀኑባቸው ሀገራት ለአካላዊ ጥቃት እና ለስነልቦናዊ ጫና ተጋላጭ እንደሚሆኑ በተደጋጋሚ የሚጠቀስ ሲሆን፣ በመንግሥት በኩል በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።
ዜጎችን ወደ ሀገር ውስጥ ከመመለስ ባሻገር፣ ከደረሰባቸው ችግር አንጻር ከፍተኛ የስነልቦና ድጋፍ ስለሚፈልጉ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ዜጎቹ ተገቢውን የስነልቦና ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለመፍጠር ስምምነት አድርጓል።
ይህ ስምምነት በውጭ አገር ለደረሰባቸው ሰብዓዊና ስነልቦናዊ ጉዳት መፍትሄ ለመስጠት እና ዳግም በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀላቅለው የተሻለ ኑሮ እንዲመሩ ለመደገፍ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ