መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚከበሩ እንደ ኢሬቻ እና መስቀል ያሉ በዓላት ማህበራዊ ትስስርን ከማጠናከር ባሻገር የቱሪዝም ፍሰትን በመጨመር ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገለፀ።
ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው።
የኢሬቻን በዓል አስመልክቶ በተደረገው በዚህ ውይይት፣ በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶታል። በውይይቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ከአዲስ አበባ እና ከሸገር ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ የበርካታ ብሄሮች እና ብሄረሰቦች መኖሪያ እንደመሆኗ፣ የተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ክንውኖች በስፋት ይስተናገዳሉ። ከነዚህም መካከል የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት ዋነኞቹ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ እነዚህን በዓላት በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ ማስመዝገቧ ይታወቃል።
እነዚህ በዓላት የቱሪዝም መስህብ ከመሆናቸውም በላይ የህዝቦችን አንድነት እና ትስስር የሚያጠናክሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ