መስከረም 14 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታይዋን ደሴት ላይ በሚገኝ አንድ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ግድብ በመፍረሱ ምክንያት በደረሰው አደጋ 17 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ። ግድቡ የተበላሸበት ምክንያት እስካሁን በግልጽ ባይታወቅም፣ ከፍተኛ ዝናብ እና አውሎ ንፋስ ለአደጋው መከሰት ምክንያት እንደሆነ ይገመታል።
የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፣ ግድቡ ከፈረሰ በኋላ በድንገት የተለቀቀው ከፍተኛ የውሃ ፍሰት በአቅራቢያው በሚገኙ አካባቢዎች የጎርፍ መጥለቅለቅን አስከትሏል። በተጨማሪም በርካታ ቤቶች እና መሰረተ ልማቶች እንደወደሙ ተገልጿል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እና የነፍስ አድን ቡድኖች በአካባቢው ተሰማርተው የጠፉ ሰዎችን የመፈለግ እና የተጎዱትን የማንሳት ስራ እየሰሩ ነው። ባለስልጣናት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል። የአደጋው መንስኤ በዝርዝር እየተጣራ ነው።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ