መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታይላንድ የምትገኘው ሞሻ የተባለችው እስያዊት ዝሆን፣ ገና በህፃንነቷ እንቅስቃሴ ላይ በነበረችበት ጊዜ በተቀበረ ቦምብ ፍንዳታ ሳቢያ እግሯን ብታጣም፣ በዓለማችን የመጀመሪያዋ ሰው ሠራሽ እግር የተገጠመላት ዝሆን በመሆን የፅናትና የድል ተምሳሌት ሆናለች።
በታይላንድ የሚገኘው እና ‘የእስያ ዝሆኖች ወዳጆች’ የተሰኘው የእንስሳት ሆስፒታል፣ ይህች አደጋ የደረሰባት ዝሆን ከባድ ህመም እንዳይሰማትና ህይወቷን እንድትቀጥል ለመርዳት ልዩ ጥረት አድርጓል። ሆስፒታሉ በመላው ዓለም ካሉ ተመራማሪዎች ጋር በመተባበር ለዝሆኗ የመጀመሪያውን ሰው ሠራሽ እግር በመስራት ለመስጠት ችሏል። ይህ በመላው ዓለም ለዝሆን የተሰራ የመጀመሪያውና አዲስ የህክምና ፈጠራ ነው ተብሏል።
ዝሆኗ በየጊዜው እያደገች ስትሄድም፣ የሰውነቷ ክብደትና መጠን እየጨመረ ስለሚሄድ፣ ለእግሯ ትክክለኛውን ክብደት ሊሸከም የሚችል አዲስ እግር ደጋግሞ መተካት አስፈልጓል። የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎችም ሁኔታዋን በጥንቃቄ በመከታተል፣ ሁልጊዜም ከሰውነቷ እድገት ጋር የሚመጣጠኑ አዳዲስ ሰው ሠራሽ እግሮችን እየሰሩላት ይተክሉሏታል ተብሏል።
የዝሆኗ ታሪክ የሰው ልጅ ለእንስሳት ያለውን ታላቅ ደግነትና የዝሆንን ታላቅ የመኖር ፍላጎት በግልጽ የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን የዝሆኗ ታሪክ አደጋ የደረሰባቸው እንስሳትም ቢሆኑ ተስፋ እንደሌላቸው ሳይሆን በተገቢው እንክብካቤ እና ድጋፍ ህይወታቸውን በተሻለ መልኩ መምራት እንደሚችሉ የሚያስተምር በመሆኑ እጅግ የሚያበረታታ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ