መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የጃፓን ተመራማሪዎች ኢንተርኔት በብርሃን ፍጥነት ማስተላለፍ የሚያስችል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። ተመራማሪዎቹ በሴኮንድ 402 ቴራቢት (Tbps) በሚደርስ ፍጥነት መረጃን በማስተላለፍ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል። ይህ ፍጥነት መላውን የኔትፍሊክስ (Netflix) የቪዲዮ ስብስብ በአንድ ሰከንድ ውስጥ ለማውረድ የሚያስችል ነው ተብሏል።
ይህ ስኬት የተገኘው እጅግ ዘመናዊ የኦፕቲካል ፋይበር ኬብሎችን እና የላቀ የዳታ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ነው። ተመራማሪዎቹ ባለብዙ-ኮር (multi-core) ኬብሎችን በመጠቀም በርካታ የብርሃን ጨረሮችን በአንድ ጊዜ በማስተላለፍ ፍጥነቱን ከፍ ማድረግ ችለዋል።
የጃፓን ብሔራዊ የመረጃና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተቋም (NICT) ያከናወነው ይህ የምርምር ሥራ፣ ለወደፊቱ ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት መሠረተ ልማት ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠበቃል። የኢንተርኔት ፍጥነት ችግርን ሙሉ በሙሉ የሚቀርፍ እና ቪዲዮዎች ያለመቆራረጥ እንዲታዩ የሚያስችል አዲስ ዘመን መጀመሩን አመላካች ነው ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ገልጸዋል።
ይህ አዲስ ግኝት ቀደም ሲል የነበሩትን ሪከርዶች የደመሰሰ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለቴሌኮም ዘርፍ አዲስ ተስፋን ፈጥሯል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 🔊 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
ምላሽ ይስጡ