ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ላስ ቬጋስ ውስጥ በርገር ኪንግ ውስጥ ለ27 አመታት አንድም ቀን ሳይቀር የሰራ አንድ ሰራተኛ በሰራው ታማኝነት ከ400,000 ሺህ ዶላር በላይ የገንዘብ እርዳታ ተሰጠው።
ኬቨን ፎርድ የተባሉት ይህ ሰራተኛ ለረጅም አመታት ያሳዩትን ቁርጠኝነት እና ትጋት ለማመስገን ልጃቸው በGoFundMe ላይ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ከፈተች። ኩባንያው በ27 አመታት የስራ ዘመናቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሰጣቸው ስጦታ አነስተኛ እንደሆነ የተሰማቸው ብዙ ሰዎች ለዚህ ዘመቻ በገንዘባቸው በመለገስ ድጋፋቸውን አሳይተዋል ነው የተባለው።
በሺዎች የሚቆጠሩ ለጋሾች በኬቨን ታሪክ ተነሳስተው የገንዘብ እርዳታ ያበረከቱ ሲሆን፣ ይህም ታማኝነት እና ጠንክሮ መስራት ምን ያህል ዋጋ እንደሚሰጠው የሚያሳይ ነው ተብሏል።
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ