ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ የነበሩትና ከሞላ ጎደል ሊጠፉ የደረሱት የኖርዝ ሮናልድሴይ በጎች በብሪታንያ ወደ ነበሩበት ቁጥራቸው ተመልሰዋል እየተባለ ነው።
እነዚህ የበጎች ዝርያዎች የተገኙት በስኮትላንድ ኦርክኒ ደሴቶች ሲሆን በዘረመል ልዩ ናቸው ተብሏል። ብዙዎቹም በአራት ቀንዶች የሚታወቁ ሲሆን ይህም ያልተለመደ የዘረመል ባህሪ ነው ተብሏል።
ከሌሎች በጎች የሚለያቸው ነገር ቢኖር የአመጋገብ ልማዳቸው ነው የተባለ ሲሆን እነሱ ሳር ከመብላት ይልቅ በዋናነት የባህር አረም ይመገባሉ ተብሏል። ይህ የአመጋገብ ለውጥ በ1830ዎቹ የተከሰተ ሲሆን፣ አንድ የድንጋይ ግድግዳ ተገንብቶ ከውስጥ ያሉትን የግጦሽ መሬቶች እንዳይደርሱባቸው ከተደረገ በኋላ ነው ተብሏል።
በዚህም ምክንያት በድንጋያማው የባህር ዳርቻ ላይ እንዲኖሩ በመገደዳቸው በጊዜ ሂደትም የባህር አረም በመመገብ ራሳቸውን ማላመድ ችለዋል ነው የተባለው።
የምግብ መፈጨት ስርዓታቸውም ቢሆን በሌሎች እንስሳት ላይ የማይታይ ለውጥ አሳይቷል የተባለ ሲሆን ይህም በባህር አረም ውስጥ የሚገኘውን ከፍተኛ መጠን ያለው አዮዲን ያለ ምንም ችግር እንዲያስተናግዱ አስችሏቸዋል ነው የተባለው።
ምንም እንኳን በአንድ ወቅት እየቀነሰ በመጣው የህዝብ ብዛት እና የመኖሪያ አካባቢ ውስንነት ምክንያት ለአደጋ ቢጋለጡም፣ በተደረጉ የጥበቃ ጥረቶች እና የዘር ማሻሻያ ፕሮግራሞች አማካኝነት ቁጥራቸውን መልሰው ማግኘት ተችሏል ነው የተባለው።
በጎቹ ከሰሜን አውሮፓ ጥንታዊ የቤት እንስሳት ዝርያዎች እና ከቫይኪንግ ዘመን ጋር የተያያዘ ህያው ትስስር ያላቸው በመሆናቸው ይከበራሉ ተብሏል።
መመለሳቸውም ለብዝሀ ሕይወት፣ ለእርሻ እና ለባህላዊ ቅርስ ትልቅ ድል ነው ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
በጌታሁን አስናቀ
ምላሽ ይስጡ