ነሐሴ 14 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) 12 ሃገራት የሚሳተፉበት የዘንድሮውን የ2025 የምስራቅ፣ ማዕከላዊና የደቡብባዊ አፍሪካ ሃገራት የዓይን ህክምና ኮሌጅ ማህበራት ህብረት ጉባዔ እየተካሄደ ይገኛል።
ከሰሜን አሜሪካ፣ ከአውሮፓና ከእስያ ከጤና ሳይንስ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች የተዉጣጡ የዓይን የህክምና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት እንደሆነም ብርሃን የህብረተሰብ ጤናና የዓይን እንክብካቤ አማካሪው ዶ/ር ወንዱ አለማየሁ በመድረኩ ላይ ገልጸዋል፡፡
ሃገራችንን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ከሌሎቹ የአለም ሃገራት አንጻር ሲታይ ከፍተኛ የሆነ ከፍተት ያለበት እንደሆነ አመላክተው ይህንን ችግር ለመፍታትም መንግስተን ጨምሮ የጋራ ስራን የሚጠይቅ መሆኑን ዶ/ር ወንዱ ገልጸዋል፡፡
የዓይን ማዝ በዋናነት የሚያጠቃው በእድሜ የገፉ እናቶችን መሆኑን የገለጹት አማካሪዉ፣ በንፅህና ችግር ምክንያት የሚመጣ በሽታ መከላከል እየተቻለ ትኩረት ያለው ስራ ስላልተሰራበት የመጣ ችግር ስለሆነ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዉ በ2030 የዓይን ህመምን ለመቅረፍ መሰል ኮንፍረንሶች መዘጋጀታቸው ለሃገራችን ጠቃሚ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ