
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ነዳጅ ለመቅዳት በርካታ አሽከርካሪዎች ረጃጅም ሰልፎችን መጠበቅ እየተለመደ መጥቷል በመላት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ ይህን እንግልት ለማስቀረት ሁለቱ የነዳጅ ማደያዎች አዲስ ወረፋ መጠበቂያ ስርአት መዘርጋታቸውን የኢትዮጵያ ከባድ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች ማህበር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል።
ማህበሩ ከነዳጅ አስመጪዎች ጋር በመሆን የወረፋ አያያዝ ስርዓቱን ለማሻሻል የጠየቀ ቢሆንም ኦይል ሊቢያና ቶታል ኢነርጂ ብቻ ፍቃደኛ እንደሆኑለት የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ ተናግረዋል፡፡ በወቅቱ ስምምነቱ የተደረገው ከሁለቱ ተቋማት ጋር ቢሆንም ከአዲስ አበባ ወጪ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ግን በወረፋ ስርዓቱ ላይ አለመስማማታቸውን ገልፀዋል፡፡
ስርአቱ የአሽከርካሪዎችን ደህንነትና ወጪ የሚቀንስ መሆኑን ያነሱት ሥራ አስኪያጁ፤ የተወሰኑ አሽርካሪዎች ባለመስማማታቸው ምክንያት ኦይል ሊቢያ ወደ ቀድሞ ስርዓቱ እንደሚመለስ በደብዳቤ ማስታወቁኑም ጠቅሰዋል፡፡
አሁንም እስከ ሦስት ወር ድረስ የሚቆይ ወረፋ መኖሩን የሚናገሩት የማህበሩ ሥራ አስኪጅ አቶ ሰለሞን ዘወዱ፤ በነዳጅ ዘርፍ 4ሺህ 700 የሚሆኑ ከባድ ተሽርካሪዎች ወረፋ እየጠበቁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
አሁንም ወረፋውን ማሳለጥ የማይቻል ከሆነ ተሽከርካሪ በበዛ ቁጥር ወረፋው እየጨመረ እንደሚመጣ ዋና ሥራ አስኪያጁ አንስተው፤ በፊት ላይ የአውሮፕላን ነዳጅ የሚቀዱ አሽከርካሪዎች በደረሱበት ሰዕት ይቀዱ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ እስከ አስር ቀናት ድረስ ወረፋ እንደሚጠበቁ ገልፀዋል፡፡
በጅቡቲ ባለው ሙቀት ምክንያት በበጀት አመቱ የሞቱ አሽከረርካሪዎች መኖራቸውን በማስታወስ አሁን ላይ አሽከርካሪዎች በሚያደርጉት ጥንቃቄ ችግሩ መቀነስ መቻሉን አመላክተዋል፡፡
ምላሽ ይስጡ