ነሐሴ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም ዙሪያ የንቦች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ ምክንያት በሰብል ምርት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመከላከል ጃፓን አነስተኛ መጠን ያላቸውን ሮቦት ንቦች መፍጠር መጀመሯን አስታውቃለች።
እነዚህ ጥቃቅን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የሚመሩ ድሮኖች በአበቦች መካከል የአበባ ዘርን ለማሰራጨት የሚያስችላቸው ካሜራ እና ለስላሳ ፀጉር በታጣፊ ጄል ተሸፍኖባቸዋል ነው የተባለው።
ይህ ቴክኖሎጂ አበቦችን ለይቶ ማወቅ፣ የአበባ ዘርን መሰብሰብ እና ከእጽዋት ወደ እጽዋት ማስተላለፍ የሚችል በመሆኑ የተፈጥሮ ሂደቱን ለመምሰል ታስቦ የተሰራ ነው ተብሏል።
በአሁኑ ጊዜ በሙከራ ላይ የሚገኘው ይህ ቀላል ክብደት ያለው ቴክኖሎጂ፣ ሰብሎችን ሳይጎዳ የአበባ ዘርን ለማሰራጨት ታስቦ የተሰራ ሲሆን፣ የአበባ ዘር አስፋፊዎች ከፍተኛ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች የዓለምን የምግብ ምርት ለመጠበቅ እንደ አንድ መፍትሄ ሊያገለግል እንደሚችል ታሳቢ ተደርጓል።
ይህ ቴክኖሎጂ ገና በምርምር እና በልማት ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ሰው የሚዘራውን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት ሳይሆን የንቦች ቁጥር እጥረት በሚያጋጥምበት ጊዜ እንደ ረዳት መፍትሄ ለመጠቀም ያለመ ነው ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ