ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) አዲስ የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ወንዶች በዓመት በአማካይ ሰባት ሰዓታትን የሚጠቀሙት በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ነው፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ለንፅህና ሳይሆን ከውጥረትና ከቤተሰብ ግርግር እረፍት ለመውሰድ ነው ተብሏል።
የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው፣ ብዙ ወንዶች መታጠቢያ ቤትን ለራሳቸው ሰላማዊ ቦታ አድርገው ይቆጥሩታል ነው የሚለው። ከዕለት ተዕለት የቤት ውስጥ ስራዎች፣ ከልጆች ወከባ፣ ወይም ደግሞ ከትዳር ጓደኛ ጋር ከሚፈጠር ውጥረት ለመራቅ ይህንን ቦታ እንደ መጠለያ ይጠቀሙበታል ነው የተባለው።
ተመራማሪዎቹ እንዳረጋገጡት፣ ይህ በመታጠቢያ ቤት ውስጥ የሚጠፋው ጊዜ መፀዳጃ ቤትን ከመጠቀም በተጨማሪ፣ ስልካቸውን ለማየት፣ ለብቻቸው ለማሰላሰል፣ ወይም ዝም ብሎ ለመቀመጥ እንደሚያገለግል ተገልጿል።
ይህ ግኝት ብዙ ወንዶች በቤት ውስጥ የሚያጋጥማቸውን ጫና እና የሚፈልጉትን የግል ጊዜ ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ምላሽ ይስጡ