ነሐሴ 08 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በበጀት አመቱ የተበላሹና ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመዋቢያ ምርቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
የተለያየ ችግር የታየባቸው ከ1መቶ 96ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የውበት መጠበቂያዎች መሰብሰባቸውን የተናገሩት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተበላሹና ደረጃቸውን ያልጠበቁ የመዋቢያ ምርቶች በቁጥጥር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
በበጀት አመቱ ለ170 የውበት መጠበቂያ ምርቶች ፈቃድ መሰጠቱን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ መስፈርቱን ላሟሉ 16 አዲስ የመዋቢያ ምርት አምራቾች እና 104 አስመጪና አከፋፋዮች ድርጅቶች የቅድመ ፈቃድ ኢንስፔክሽን በማከናወን የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት መቻሉን ገልፀዋል፡፡
በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ላይ የውበት መጠበቂያን የሚያስተዋውቁ በርካቶች በመሆናቸው ማህበረሱቡ ፍቃድ ከሌላቸው አካላት ባለመግዛት ራሱን እንዲጠብቅ ጠቁመዋል፡፡
በመድኃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያ ተቋም በሆኑ 227 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ 105 እገዳ፣ 32 ስረዛ፣ 66 እሸጋ እርምጃዎች መወሰዱን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በመድኃኒት አስመጪና አከፋፋዮች ላይ 162 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፤ 62 እገዳ፤ 18 ስረዛ ፣ 20 እሸጋ መከናወኑን ያነሱት ዳይሬክተሯ፤ በመድኃኒትና የህክምና መሳሪያ አስመጪ /ጅምላ አከፋፋይ/ ላይ 11 እገዳ ፤ በመድኃኒት መደብር 4 የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ በመድኃኒት ቤት 2 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያና 11 እገዳ፤ በመድኃኒት ችርቻሮ ቤቶች 53 የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ 4 እገዳ ፣ 4 ስረዛ እንዲሁም 52 የእሽጋ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በዛሬው እለት የ2017 በጀት አመት አፈፃፀሙን ሪፖርት አቅርቧል፡፡
ምላሽ ይስጡ