ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ጃይር ቦልሶናሮን በቁም እስር እንዲቆዩ ያዘዘ ሲሆን፤ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው እ.ኤ.አ. በ2023 በተካሄደው የመንግስት መገልበጥ ሙከራ ሴራ ውስጥ ተሳትፈዋል በሚል ክስ ነው ተብሏል።
በብራዚሊያ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ በቦልሶናሮ ደጋፊዎች የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ፣ ፍርድ ቤቱ የቀድሞው ፕሬዝዳንት በወንጀሉ ውስጥ እጃቸው እንዳለ በመጠርጠር ምርመራ ሲያደርግ ቆይቷል ነው የተባለው። ጃይር ቦልሶናሮ ግን ሁሉንም ክሶች እየካዱ ነው ተብሏል።
በውሳኔው መሰረት፣ ቦልሶናሮ ከቤት የመውጣት መብታቸው የተገደበ ሲሆን፣ ያለፍርድ ቤቱ ፈቃድ ከከተማ ወጣ ብለው መሄድ አይችሉም ተብሏል። ጠበቆቻቸው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቃውመው ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል።
ይህ ውሳኔ በብራዚል ፖለቲካ ውስጥ ውጥረትን የፈጠረ ሲሆን፣ ደጋፊዎቻቸው እና ተቃዋሚዎቻቸው የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ነው ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ