ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በብራዚል የምትገኝ አንዲት ላም በአንድ ቀን ውስጥ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወተት መጠን በማምረት የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧ ተገለጸ።
ላሟ በ24 ሰዓታት ውስጥ 123.61 ሊትር ወተት በማምረት በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ በይፋ መረጋገጡ ታውቋል።
ይህ አስደናቂ ስኬት የዘመናዊ የእንስሳት እርባታ ቴክኖሎጂ እና የጄኔቲክስ መሻሻል ውጤት መሆኑን ተገልጿል። ላሟ ለዚህ ታላቅ ምርት እንድትበቃ የተደረገው በተራቀቀ የመመገብ ዘዴ፣ የጤና ክትትል እና የዘረመል ምርጫ አማካኝነት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡
የዚህ ክብረወሰን መመዝገብ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ የወተት አምራቾች ትልቅ መነሳሳት የሚሰጥ ሲሆን፣ የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ምን ያህል ሊቀጥል እንደሚችል ማሳያ ሆኗል ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ