ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በሳይንሳዊ ዘርፍ የተደረገ አንድ ጥናት አስገራሚ ግኝት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ከወንዶች ብብት ላብ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካላዊ ምልክቶች የሴቶችን ሆርሞን ሊነኩ ይችላሉ ተብሏል።
ይህ ግኝት እንደሚያሳየው፣ እነዚህ ኬሚካላዊ ምልክቶች (pheromones) የሴቶችን የወር አበባ ዑደት ከማስተካከል በተጨማሪ፣ ስሜታቸውን የማሻሻል አቅም አላቸው ተብሏል።
የጥናቱ ተመራማሪዎች ይህ ግኝት የሰው ሆርሞን በስሜታዊ እና ባዮሎጂያዊ ምላሾች ላይ ያለውን ኃይለኛ ተጽዕኖ እንደሚያጎላ ገልጸዋል።
ይህ ጥናት በሰው ልጆች መካከል ባለው የባዮሎጂያዊ መስተጋብር ላይ ያለንን ግንዛቤ ከፍ የሚያደርግ ሲሆን፣ ለዚህ ዘርፍ አዲስ እይታ የሚሰጥ ነው ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ