👉50 ያክሉት ደግሞ ጠፍተዋል ሲል IOM ገልጿል
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) እንደገለጸው፣ ከሊቢያዋ ቶብሩክ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በደረሰ አደጋ የ18 ስደተኞች ህይወት አልፏል፤ የ50 ያህል ስደተኞች ደግሞ እስካሁን የት እንደደረሱ አይታወቅም ብሏል።
አደጋው የተከሰተው ስደተኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በመስመጥ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን የጠፉትን ሰዎች የማፈላለግ እና የማዳን ስራ እየተካሄደ መሆኑን ድርጅቱ አስታውቋል።
ይህ አደጋ አደገኛ በሆኑ የባህር ላይ ጉዞዎች በየጊዜው ለሚከሰተው የስደተኞች ህይወት መጥፋት ሌላኛው አሳዛኝ ምሳሌ ነው ተብሏል።
አይ.ኦ.ኤም. በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰው እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ