ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ደቡብ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ ተሰቅለው የነበሩ የድምፅ ማጉያዎችን የማፍረስ ሥራ መጀመሯን አስታውቃለች።
ይህ እርምጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ለመቀነስ ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
ይህ የማፍረስ እርምጃ የተወሰደው፣ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ባለፈው ሰኔ ወር የድምፅ ማጉያዎቹ ስርጭት እንዲቆም ከሰጡት ትዕዛዝ በኋላ ነው ተብሏል።
የድምፅ ማጉያዎቹ ለዓመታት ለሰሜን ኮሪያ የፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ እንደነበር ይታወቃል።
የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/menaharia_fm
__
ምላሽ ይስጡ