ሐምሌ 25 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሕክምና ሳይንስ እና በቴክኖሎጂ መካከል ያለውን ድንበር የሚገፋ ታሪካዊ ክስተት ተመዝግቧል። ኦድሪ ክሩስ የምትባል ከ20 ዓመታት በላይ ፓራላይዝድ ሁና ስትሰቃይ የነበረች ሴት፣ የአእምሮዋን ትዕዛዝ በመጠቀም ስሟን በኮምፒዩተር ስክሪን ላይ ለመጻፍ ችላለች ተብሏል። ይህ አስደናቂ ስኬት እውን የሆነው በኤሎን መስክ ኒውራሊንክ ኩባንያ የተገነባውን የአእምሮ ቺፕ ከተተከለላት በኋላ ነው ተብሏል።
የኒውራሊንክ ቺፕ፣ “ብሬን-ኮምፒዩተር ኢንተርፌስ” በመባል የሚታወቀው ቴክኖሎጂ አካል ሲሆን፣ የአእምሮ ውስጥ የነርቭ ሴሎች የሚያመነጩትን ምልክቶች በቀጥታ ወደ ኮምፒዩተር ትዕዛዝ ይቀይራል ተብሏል። ወይዘሮ ክሩስ ለዓመታት በእጇ መጻፍ አልቻለችም የተባለ ሲሆን፣ አሁን ግን በአዕምሮዋ ብቻ “ኦድሪ” የሚለውን ፊርማዋን መጻፍ ችላለች ተብሏል።
ይህ ክንውን የአካል ጉዳት ላለባቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን፣ የአዕምሮን አቅም ወደ ዲጂታል መረጃ የመቀየር ቴክኖሎጂ ምን ያህል እንደገፋ የሚያሳይ ማረጋገጫ ሆኖ አገልግሏል እየተባለ ነው።
ባለሙያዎች ይህ ቴክኖሎጂ ለወደፊቱ የአካል ጉዳተኞችን ህይወት በከፍተኛ ደረጃ ሊለውጥ እንደሚችል እየገለጹ ሲሆን፣ ሰዎች አዕምሯቸውን በመጠቀም ሮቦቶችንና ሌሎች የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን መቆጣጠር እንዲችሉ በር ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።
ምላሽ ይስጡ