ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ESCFE ይህ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌዴሬሽን በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአንድ ዋርካ ስር በማሰባሰብ ባህል ፤ ታሪክ እና ትውፊቶቻቸውን እንዲሁም የእርስ በእርስ ህብረ ብሄራዊነት የሚጠናከርበት የስፖርት እና ባህል ፌስቲቫል የሚከናወንበት አመታዊ ዝግጅት ነው። ይህንንም ዝግጅት እኤአ ከ2002 አንስቶ ሳይቋረጥ አመታዊ በሆነ መልኩ ሲያከናውን ቆይቷል።
ይህንኑ ተግባር ላለፉት 19 አመታት ሲያከናወን መቆየቱን የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ የፊታችን ሀምሌ 22 በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ላይ በአውሮፓ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው አመታዊ ዝግጅት ለ20ኛ ጊዜ የሚከናወን ይሆናል።
ከዝግጅቱ ጋር በተያያዘ አቶ ዘላለም ይርዳው የተቋሙ የፋይናንስ አስተዳደር ሀላፊ እና አቶ ሰለሞን አለሙ የማርኬቲንግ ክፍል ሀላፊ በጋራ በሀርመኒ ሆቴል ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ አመላክተዋል።
3 የእግርኳስ ቡድኖች ከኢትዮጵያ ወደ ጀርመን አቅንተው በውድድሩ ላይ እንደሚካፈሉ እንዲሁም በአጠቃላይ 40 እግርኳስ ቡድኖችን ጨምሮ የተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ይከናወኑበታል ተብሏል። በአጠቃላይ ዘንድሮ ከ50 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት መድረክ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል።
ይህ መድረክ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ባህል እና አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት ከመሆኑም በላይ በበጎ አድራጎት ላይ የሚሳተፉበትን እድል ይዞ የቀረበ ተቋም መሆኑ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለአንጋፋው አሰልጣኝ አስራት ሀይሌ 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ መድረጉ የተጠቆመ ሲሆን በተለያዩ የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ የሀገራችን ዜጎች ከ6 ሺ ዩሮ በላይ ገንዘብ በማዋጣት እገዛ መደረጉን አስታውቀዋል።
በዘንድሮ ዝግጅት ከ10 ያላነሱ አርቲስቶች ስራዎቻቸውን በጀርመን እንደሚያቀርቡ የተገለፀ ሲሆን ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያሉ ድርጅቶች ይህ ኢትዮጵያዊነት የሚንፀባረቅበት መድረክ ላይ ምርት እና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ተጋብዘዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን 📞
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ