👉በዜሮ ነዳጅ፣ በዜሮ ልቀት 40,000 ኪሎሜትሮችን በአንድ ጊዜ መብረር ያስችላታል ነው የተባለው
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአቪዬሽን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው “ሶላር ኢምፐልስ 2” (Solar Impulse 2) የተሰኘው ልዩ አውሮፕላን፣ ነዳጅ ሳይጠቀም እና ምንም ዓይነት ካርቦን ወደ ከባቢ አየር ሳይለቅ፣ በመላው ዓለም ዙሪያ ታሪካዊ ጉዞውን ማጠናቀቁ ተዘግቧል።
ይህ በአንጋፋዎቹ ስዊስ አብራሪዎች በበርትራንድ ፒካርድ (Bertrand Piccard) እና በአንድሬ ቦርሽበርግ (André Borschberg) የሚመራው ፕሮጀክት፣ ከ40,000 ኪሎሜትር በላይ ርቀትን በንጹህ የፀሐይ ኃይል ብቻ በመጓዝ የዘላቂ ቴክኖሎጂዎችን እምቅ አቅም በተጨባጭ አሳይቷል ተብሏል።
“ሶላር ኢምፐልስ 2” በንድፉ እና በቴክኖሎጂው እጅግ ልዩ ነው የተባለ ሲሆን፤ግዙፍ ክንፎቹ በሺዎች በሚቆጠሩ የፀሐይ ፓነሎች የተሸፈኑ ሲሆን፣ እነዚህ ፓነሎች በቀን ውስጥ ኃይል በማመንጨት አውሮፕላኑ እንዲበር ያስችሉታል ነው የተባለው።
ከመጠን በላይ የሚመነጨው ኃይል ደግሞ አውሮፕላኑ በሌሊት ለመብረር የሚያስችሉትን ባትሪዎች ይሞላል ነው የተባለው።
ይህ ንድፍ አውሮፕላኑ ቀንም ሆነ ሌሊት ያለማቋረጥ እንዲበር አስችሎታል የተባለ ሲሆን፤እጅግ ቀላል ክብደት ባላቸው ቁሳቁሶች የተሰራ መሆኑ እና ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ሞተሮች መጠቀሙ ለዚህ ታሪካዊ ስኬት ዋና ምክንያቶች ተብለዋል።
አቡዳቢን የመነሻና መድረሻ አድርጎ የተከናወነው ይህ የዓለም ዙርያ በረራ፣ በተለያዩ ደረጃዎች ተከፍሎ ከአንድ ዓመት በላይ ፈጅቷል።
ከጉዞው ፈታኝ ክፍሎች መካከል የአምስት ቀናት ከሌሊት የማያቋርጥ የአብራሪዎች በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ያደረጉት በረራ ይጠቀሳል ነው የተባለው።
ይህ በረራ በአውሮፕላን ታሪክ ከነዳጅ ነፃ የሆነ ረጅሙ ነጠላ በረራ ሲሆን፣ የአብራሪዎቹን አካላዊና አእምሯዊ ጥንካሬም ጭምር የፈተነ ነበር ተብሎለታል።
በመንገዱ ላይ በተለያዩ ከተሞች ማረፍ የቴክኖሎጂውን አቅም ለማሳየት እና የአካባቢ ጥበቃ መልዕክትን ለማስተላለፍ አስችሏል ነው የተባለው።
የ”ሶላር ኢምፐልስ 2″ ስኬት ከምንም በላይ ለንጹህ፣ ታዳሽ ኃይል በአቪዬሽን ዘርፍ ያለውን ትልቅ አቅም ያሳየ ነው የተባለ ሲሆን፤ ይህ ፕሮጀክት ነዳጅ አልባ በረራ ሊሳካ እንደሚችል ማረጋገጡ ብቻ ሳይሆን፣ ሳይንቲስቶችን እና መሐንዲሶችን ቀጣይ ትውልድ ንጹህ ኃይል ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች እንዲያዳብሩ አነሳስቷል ተብሎታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ