ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ብሄራዊ ባንክ ከመጋቢት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ጀመሮ በየሁለት ሳምንት ሲያካሂደ የነበረው የውጪ ምንዛሬ ጨረታ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ መጠናቀቁን ብሄራዊ ባንክ ለጣቢያችን አስታውቋል።
ለተከታታይ አራት ወራት ሳይቋረጥ ጨረታው መካሄዱን የሚገልጹት የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዥ እና ዋና ኢኮኖሚስት አቶ ፍቃዱ ድጋፌ ናቸው።ምክትል ገዢው እንደሚገልጹት በየ15 ቀናት ሲካሄድ በጨረታ መመሪያ መሰረት ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ያስገባ ባንክ አሸናፊ በመሆን 420 ሚሊየን ዶላር ከብሄራዊ ባንክ ለባንኮች መሸጡን ገልጸዋል።
በጨረታ ሂደቱ ላይ የተነሱ ቅሬታዎች ከባንኮች አለመኖራቸውን የገልጹት አቶ ፍቃዱ ግልጽ በሆነ አሰራር እና መመሪያ መሰረት ጨረታው መካሄዱንና ከፍተኛ የጨረታው የአንድ ዶላር ዋጋ 136 ብር መሆኑንም ተናግረዋል።
በተጨማሪም ከተጀመረ ጀምሮ በተከታታይ ሳይቋረጥ መቀጠሉ እና ግልጽ በመሆኑ በውጪ ምንዛሬ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በተለይም እጥረቱ አሁን ላይ መቃለሉን ጠቁመዋል።
እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሳይቋረጥ እንደሚካሄድ የተገልጸው ጨረታው መጠናቀቁን ተከትሎ በ2018 በጀት አመት ላይ ቀጣይነቱን በሚመለከት ብሄራዊ ባንክ የሚገልጽ መሆኑ የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ፍቃዱ ድጋፌ አመላክተዋል።
__
ምላሽ ይስጡ