ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የፌዴራል የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ይፋዊ ውይይት መድረክ በምክር ቤቱ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬዉ እለት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ መንግስት ከማክሮ ኦኮኖሚው ማሻሻያ በኋላ ለመንግስት ሰራተኞች ወርሃዊ ደሞዝ ክፍያ ቢያሻሽልም ሰራተኛው በፊተት ከነበረበት የኑሮ ሁኔታ በላይ ቁልቁል እየወረደ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ደመወዛቸው ተሸሽሏል ቢባል አሁንም በተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ለልመና እየተዳረጉና በቀን አንድ ጊዜ መብላት የማይችሉበት ደረጃ ላይ በመሆናቸው አሁንም የዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሊወሰን ይገባል ሲሉ ጥያቄያቸዉን አቅርበዋል፡፡
በተለይም አሁን ላይ ያለው የገቢ ግብር አካል ጉዳተኛውን እጅግ እየፈተነው እንደሆነ በምክር ቤቱ የተናሩት ደግሞ የኢትዮጵያ ምሁር አይነስውራን ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር በቀለች ጥሩዬ ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ያለው የኑሮ ውድነት በኛ ሃገር ብቻ የሚታይ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ነው የሚሉት ደግሞ ከምክር ቤቱ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ሆረታ ናቸው፡፡ የኑሩ ውድነቱ ከወርሃዊ ክፍያ ጋር ብቻ ሊያያዝ አይገባ ያሉት ሚኒስቴር ዲኤታው የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥም ሊፈተሸ እንደሚገባ አንስተው፤ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በኋላ የተደረገው የደሞዝ ማሻሻያና አሁንም የገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የቀረበው ረቂቅ አዋጅ በጥናት ተደገፈ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የታክስ ግብሩን በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በቋሚ ኮሚቴ ደረጃ ከፍተኛ የሆነ ጥያቄ እንደሚቀርብ የተናገሩት የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር አብርሃም አለማየሁ ከምክር ቤቱ የተነሱ የባለድርሻ አካላት ሃሳብ አንድ ግብዓት መሆኑን ተናግረዋል፡ በግብር ክፍያ በኩል ከፍተኛ የሆነ ጫና ሲደርስባቸው የነበሩ አካላትን መለየት በቅድሚ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
ምክር ቤቱ የመንግስትንም የህዝብንም ፍላጎት በማጣጣም ረቂቁን ለማሻሻል እደሚሰራና አሁን ተሻሽሎ የቀረበው ረቂቅ ምን ያህል ተሸሽሏል የሚለውን በተረጋጋ መንገድ ቋሚ ኮሚቴው ጥናት ያደረጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ