ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ መርሀ-ግብራቸው እንዲሸጋሸግ ለፕሪሚየር ሊጉ ያስገቡት ደብዳቤ ውድቅ ተደረገ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክለቦች የአለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ነው። የፊታችን እሁድ ከፓሪስ ሴንት ጄርሜ ጋር ጨዋታቸውን Metlife stadium ላይ የሚናደርጉ ይሆናል።
ታዲያ ይሄንን ጨዋታ ካከናወኑ ከ34 ቀናት በኋላ ተወዳጁ እና ብርቱ ፉክክር ያለበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቀጣዩ የ2025/26 የውድድር ዘመንን በለንደን ደርቢ ከክሪስታል ፓላስ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ በይፋ የሚጀምሩ ይሆናል።
ስለዚህ ተጫዋቾች እረፍት እንዲያገኙ እና የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውንም በ1 ወር ውስጥ ለማከናወን ይገደዳሉ ማለት ነው ፤ ያንን ተከትሎ የሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታቸው እንዲሸጋሸግ ለፕሪሚየር ሊጉ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የኤንዞ ማሬስካው ቡድን ጫና ውስጥ የከተተ ውሳኔ ሆኗል። ቼልሲ የፊታችን እሁድ ፓሪስ ሴንት ጄርሜን በመርታት የክለቦች የአለም ዋንጫን ማሳካት ከቻሉ 97 ሚሊዮን ፓውንድ የሚያገኙ ይሆናል።
ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ ላሊጋው አስተዳደር ከዛ ውጪ እንደ ማንቸስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮሊ እና ሌሎችም የክለቦች የአለም ዋንጫ ተለጥጦ በዚህ ሰአት መደረጉ የቀጣዩን የውድድር ዘመን እና ተጫዋቾች ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ አልገባም በማለት የውድድር መድረኩን መተቸታቸው አይዘነጋም።
ምላሽ ይስጡ