ሰኔ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ ልዩ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 በጀት አመታዊ ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡ በበጀት አመቱ ምክርቤቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ ወሳኝ የሚባሉ የህግ ማእቀፎችን ያወጣ ቢሆንም ህግና መመሪያውን ከማውጣት ባሻገር አፈፃፀሙን የማይገመግም በመሆኑ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን እያሳደረ መሆኑን አባላቱ ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ሦስት አመታት የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄ የነበሩ ጉዳዮች በአራተኛ አመት የስራ ዘመኑ ላይም ጥያቄ ሆነዉ መቀጠላቸዉን ያነሱት አባላቱ በምክር ቤቱ በአባላቱ የሚነሱ ጥያቄዎች የህዝብ ጥያቄዎች በመሆናቸው በየጊዜው ሊፈቱ እንደሚገባና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አካታችነት እንደጎደላቸው ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ተቋማት በየወቅቱ ጊዜያዊ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ፤ በማያቀርቡና የማይገኙ አመራሮች ላይ ምክር ቤቱ እርምጃን እንዲወስድ በአባለቱ ተጠይቋል፡፡
የምክር ቤቱ አበላት ስፊ ስራ የሚጠበቅባቸው ቢሆንም የሚከፈላቸው ወርሃዊ ክፍያና የውሎ አበል በቂ ባለመሆኑና በምክር ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለተመረጡ ተፎካካሪ ፖርቲዎች የራሳቸው ቢሮ ቢዘጋጅላቸው ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
በ2017 በጀት አመት ምክር ቤቱ ለሃገር እድገት ወሳኝ የሚባሉ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የምክር ቤቱ አባላት የደመወዝ ጥያቄ የሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ጥያቄ በመሆኑ በምክር ቤቱ ብቻ የሚወሰን እንዳልሆነ አንስተው በምክር ቤቱ የሚወጡ የህግ ማዕቀፎች የሚታዩ ቢሆንም አሁን የሚቀሩ ነገሮች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡ ለምክር ቤቱ በወቅቱ ሪፖርት በማያቀርቡትና በተደጋጋሚ የምክር ቤት ስብሰባዎች በማይገኙ አባላት ላይ ህጉን በጠበቀ መልኩ እርምጃ እንደሚወሰድ ወ/ሮ ሎሚ አስታውቀዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ ምክር ቤቱ ባካሄደው 43 መደበኛ ስብሰባዎችና 3 ልዩ ስብሰባዎች 56 አዋጆች ለምክር ቤቱ የቀረቡ ሲሆን 34 ለቋሚ ኮሚቴዎች ተመርቶ ይፋዊ የሕዝብ ውይይት ተደርጎ በሁለተኛ ንባብ ሲፀድቁ 15 ወደ ሁለተኛ ንባብ ተሸጋግረዉ መፅደቃቸዉን፤ ከ2016 በጀት አመት የተሸጋገሩትን 2 አዋጆችን ጨምሮ በአጠቃላይ 7 አዋጆች ወደ 2018 በጀት ዓመት መሻገራቸው ተመላክተዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
ምላሽ ይስጡ