ሰኔ 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አርኪኦሎጂስቶች በፔሩ ሰሜናዊ ባራንካ ግዛት ውስጥ ጥንታዊ ከተማ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
3ሺሕ 500 ዓመታት ዕድሜ ያስቆጠረው ፔኒኮ የተባለው ከተማ ቀደምት የፓሲፊክ የባህር ዳርቻ ማህበረሰቦችን ከአንዲስ ተራሮች እና በአማዞን ተፋሰስ ከሚገኙት ጋር የሚያገናኝ ቁልፍ የንግድ ማዕከል ሆኖ እንዳገለገለ ተገምቷል።
ሊማ ከተባለው ከተማ በስተሰሜን 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ቦታው ከባህር ጠለል በ600 ሜትር ከፍታ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከተማው የተመሰረተው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1800 እና 1500 ክፍለ ዘመን መካከል እንደሆነ ይገመታል ተብሏል።
በተጠቀሰው ተመሳሳይ ጊዜ በመካከለኛው ምስራቅ እና እስያ የጥንት ስልጣኔዎች እየተስፋፉ መሄዳቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል።
ተመራማሪዎች ግኝቱ የአሜሪካ ጥንታዊ ሥልጣኔ በሆነው ካርል ላይ አዲስ የምርምር ብርሃን እንደሚፈጥር ይናገራሉ።
በተመራማሪዎች የተለቀቀው የድሮን ምስል በከተማው መሃል ባለ ኮረብታ ላይ ክብ ቅርጽ ያለው የድንጋይ እና የጭቃ ህንጻዎች ያሳያል።
በሥፍራው በተደረገው የስምንት ዓመታት ጥናት 18 ቤተመቅደሶች እና የመኖሪያ ሕንፃዎች በቁፋሮ ተገኝተዋል ብሏል ዘገባው።
ምላሽ ይስጡ