👉የምድር ሳተላይቶችም ሊጎዱ ይችላሉ ተባለ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ቀደም ሲል ምድርን ሊመታ ይችላል ተብሎ ሲሰጋ የነበረው አስትሮይድ 2024 YR4፣ አሁን በታህሳስ 22፣ 2032 ጨረቃን የመመታት እድሉ 4.3% መሆኑን አዲስ ጥናት አስታወቀ።
60 ሜትር ስፋት ያለው ከተማን ለማጥፋት የሚያስችል ትልቅ መጠን ያለው ይህ ግጭት ከኒውክሌር ፍንዳታ ጋር እኩል የሆነ ኃይል ያስለቅቃል፤ ይህም ባለፉት 5,000 ዓመታት ውስጥ ትልቁ የጨረቃ ግጭት ይሆናል ነው የተባለው።
አስትሮይዱ የጨረቃን ቅርብ ጎን ቢመታ፣ እስከ 10 ሚሊዮን ኪሎ ግራም የሚደርስ ፍርስራሽ ወደ ምድር ከባቢ አየር ሊሳብ ይችላል። አብዛኛው ይቃጠላል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በጥይት ፍጥነት የሚጓዙ ቅንጣቶች እያደገ የመጣውን የሳተላይቶቻችንን መረብ ሊጎዱ ይችላሉ ነው የተባለው።
በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ግጭት ከመደበኛው በ1,000 እጥፍ የሚበልጥ የሜትሮ ሻወር ሊያስከትል ይችላል፤ይህም ለሰማይ ተመልካቾች የማይረሳ ትዕይንት ይሆናል ነው የተባለው።
ምላሽ ይስጡ