👉ራፋል እና ዩሮፋይተር ታይፎን በንፅፅር
ሰኔ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) እነዚህ ጀቶች የዘመናዊ የአየር ላይ ውጊያ ምሳሌዎች ሲሆኑ፣ በተለያዩ አገራት አየር ኃይል ውስጥ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ናቸው።
🔰 ራፋል (Rafale)
👉አምራች ሀገር፡ ፈረንሳይ 🇫🇷
👉ግምታዊ ዋጋ፡ 115 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር
👉ከፍተኛ ፍጥነት፡ ማክ 1.8 (ከድምጽ ፍጥነት 1.8 እጥፍ)
ራፋል በፈረንሳይ ዳሳውልት አቪዬሽን (Dassault Aviation) የሚመረት ባለብዙ-ተግባር (Multirole) የጦር ጀት ነው። ለአየር የበላይነት፣ ለመሬት ጥቃት፣ ለስለላ እና ለኒውክሌር መከላከያ ተልዕኮዎች ሊያገለግል ይችላል ነው የተባለው።
ይህ የጦር ጀት በአንድ ጊዜ ብዙ ተግባራትን ማከናወን የሚችል (omnirole) በመሆኑ ይታወቃል ተብሎለታል።
🔰ዩሮፋይተር ታይፎን (Eurofighter Typhoon)
👉አምራች ሀገራት፡ ጀርመን 🇩🇪፣ ስፔን 🇪🇸፣ ጣሊያን 🇮🇹፣ ዩናይትድ ኪንግደም 🇬🇧
👉ግምታዊ ዋጋ፡ 105 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር
👉ከፍተኛ ፍጥነት፡ ማክ 2.35 (ከድምጽ ፍጥነት 2.35 እጥፍ)
ዩሮፋይተር ታይፎን በአራት የአውሮፓ ሀገራት ጥምረት የሚመረት የላቀ ባለብዙ-ተግባር ተዋጊ አውሮፕላን ነው ተብሎለታል።
እጅግ በጣም ፈጣን ከመሆኑም በላይ፣ ለአየር-ወደ-አየር እና ለአየር-ወደ-መሬት ተልዕኮዎች ከፍተኛ ብቃት ያሳያል ነው የተባለው።
ዘመናዊ ዲዛይኑ እና ቴክኖሎጂው እጅግ የላቀ የመንቀሳቀስ ችሎታን እንደሚሰጠውም ተመላክቷል።
♻️ሁለቱም ራፋል እና ዩሮፋይተር ታይፎን በየራሳቸው ዘርፍ እጅግ በጣም የላቁ የጦር ጀቶች ናቸው ተብሏል። ራፋል በዋነኝነት በፈረንሳይ እና ሌሎች ተጠቃሚ አገራት የአየር ኃይል ውስጥ ወሳኝ ሚና ሲጫወት፣ ታይፎን ደግሞ በአውሮፓ ውስጥ የበርካታ ሀገራት የአየር ላይ ጥበቃ ዋና አካል ነው ተብሎለታል።
የፍጥነት እና የዋጋ ልዩነቶች ቢኖሩም፣ ሁለቱም ለአየር ላይ ውጊያ እና ለተለያዩ ወታደራዊ ተልዕኮዎች እጅግ አስተማማኝ መሆናቸው ተገልጿል።
ምላሽ ይስጡ