ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሕንድ ብሔራዊ አየር መንገድ የሆነው ኤር ኢንዲያ (Air India)፣ ባለፈው ሳምንት ቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኑ ላይ በደረሰው አደጋ ምክንያት በተደረጉ የደህንነት ምርመራዎች እና በተፈጠሩ የአሠራር መስተጓጎሎች የተነሳ፣ በቀጣዮቹ ሳምንታት ዓለም አቀፍ በረራዎቹን በ15 በመቶ እንደሚቀንስ አስታወቀ።
ይህ ውሳኔ በረራ AI171 ላይ የደረሰውን አሳዛኝ ክስተት ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል፡፡ይህ አደጋ 241 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን በአስር ዓመታት ውስጥ በዓለም ላይ እጅግ ገዳይ የሆነው የአቪዬሽን አደጋ ሆኖ ተመዝግቧል።
አየር መንገዱ እንዳስታወቀው ከ33ቱ ቦይንግ 787-8 እና 787-9 አውሮፕላኖቹ ውስጥ 26 በሚሆኑት ላይ ምርመራ ተጠናቋል፤ እነዚህ 26ቱም ለአገልግሎት ተፈቅደዋል ነው የተባለው።
በፈረንጆቹ እስከ ጁላይ አጋማሽ ድረስ ተግባራዊ የሚሆኑት እነዚህ የበረራ ቅነሳዎች “የአሰራር መረጋጋትን ለማረጋገጥ፣ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና በተሳፋሪዎች ላይ የሚደርሰውን ችግር ለመቀነስ” እንደሆነ ታታ ግሩፕ ባለቤትነት ያለው አየር መንገድ ገልጿል።
ቀሪዎቹ አውሮፕላኖች በቀጣይ ቀናት እንደሚመረመሩ እና በቦይንግ 777 አውሮፕላኖቹ ላይም ተጨማሪ ምርመራዎች እንደሚደረጉ የሕንድ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
👉011-639-28-52
👉011-639-37-63
(https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
የቀጥታ ስርጭት 👉 https://zeno.fm/radio/menahria-99-1-3pw1/ (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
Telegram 👉 https://t.me/menaharia_fm
ምላሽ ይስጡ